የዓፋር እና የትግራይ ህዝብ ግንኙነት ጥንታዊ መሰረት ያለው በመሆኑ በቀላሉ ጠላቶች ሊበጥሱት እንደማይችሉ የዓፋር ፌዴራሊስት ሃይል አመራሮች ገለፁ።
በአሁኑ ሰዓት የዓፋር ህዝብ ከፍተኛ ግፍ እየተፈፀመበት በመሆኑ ፌዴራሊስት ሃይሉ ከሌሎች አጋሮች ጋር በመሆን የተጨቆኑ ህዝቦችን ለማዳን እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
እንዲሁም የዓፋር ህዝብ ፓርቲ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በዓፋር እያጋጠመ ያለውን የሰብአዊ ቀውስ መፍትሄ እንዲሰጥበት አሳሰበ።
የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ በዓፋር ክልል ዋና ከተማ ሰመራ በሰጠው መግለጫ። የሰላማዊያን ሰዎች ግድያ እንዲቆምም ጠይቋል።
ፓርቲው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በዓፋር ህዝብ ላይ እየቀጠለ ያለውን ግፍ ማስቆም ባለመቻሉ የሁሉም ችግር ባለቤት በመሆኑ ሊጠየቅ እንደሚገባ ያመለከተው ፓርቲው የዓፋር ህዝብ ሉአላዊነቱን ለማስከበርና ራሱን ለመከላከል ዝግጁ መሆኑ መግለፁ የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ያስረዳል።