Home ዜና የግንቦት 20 የድል በዓል የሚከበረው ኢትዮጵያ በአለም ማህበረ-ሰብ የልማት ማእከል በመባል ተፅእኖ...

የግንቦት 20 የድል በዓል የሚከበረው ኢትዮጵያ በአለም ማህበረ-ሰብ የልማት ማእከል በመባል ተፅእኖ ፈጣሪ እንድትሆን አድርጓታል፡፡

761

ለዘመናት በሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ ተፈርዶ የነበረው ጭቆናና በደል የተረዱት የትግራይ ልጆች ከ48 አመት በፊት በደደቢት በርሀ ብሶት የወለደውን ትግል በመጀመር 17 አመታትን መራራ ትግል በማድረግ 1983 ግንቦት 20 የደርግን ስርአት በመግርሰስ ድል ተቀናጅተዋል፡፡

ለሁሉም ራስን በራስ ለማስተዳደር እና ለመወሰን የሚታገሉ ህዝቦች እኩልነትና ነፃነት የተደረገው ፈታኝ  ምእራፍ የአንበሳውን ሚና የተጫወተው የትግራይ ህዝብ እንደነበር ታጋይ ዓፈራ አሰፋ ይናገራሉ፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ህዝቦች ፍላጎት ህገ-መንግስት  መስርቶ እንዲተዳደር ከማድረግ በተጨማሪ በአለም ማህበረ-ሰብ የልማት ማእከል በመባል ተፅእኖ ፈጣሪ እንድትሆን አድርጓታል ይላሉ፡፡                                                                                                    

የትግራይ ህዝብ ባሰፈነው የህዝቦች እኩልነት በሃገሪቱ የተለያዩ ልማታዊ ድርጅቶች ተቋቁመው፤ ከድህነት አረንቃ አንዲላቀቅ ማልማት ተጀምሮ የነበረ እንኳን ቢሆንም የደርግ ስርዓት ናፋቂዎች ከባእድ ሃገራት ጋር በመወገን በደሙ ያረጋገጠውን ነፃነቱን በመድፈርና ሃብት ንብረቱን ዘርፈዋል፤ ለመዝረፍ ያልቻሉትም አውድመዋል፡፡ የትግራይ ህዝብም በዚህ ሳይንበረከክ ዳግም ታሪክ ይሰራለም ብለዋል፡፡

በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀው ዘር የማጥፋት ወንጀል ከልማታዊ ስራዎቻቸው ተስተጓጉለው ጠላትን ወደ መመከት የገቡት የትግራይ ሰራዊት አባላት፤ የግንቦት 20 ታሪክ በመድገም በትግራይ ህዝብ ላይ የተኖረውን ከበባና ክልከላ መስበር እንደማይቀርና የህዝብ ሰቆቃ ለማስቆም እስከ መስዋእትነት ዝግጁ ነን ብለዋል ፡፡