Home ዜና ኤደን ገብረመድህን ትባላች የአስር አመት ታዳጊ ስትሆን መንቀሳቀስ የማትችል የመቐለ ከተማ ነዋሪ...

ኤደን ገብረመድህን ትባላች የአስር አመት ታዳጊ ስትሆን መንቀሳቀስ የማትችል የመቐለ ከተማ ነዋሪ ናት፡፡ ገና የአንድ አመት ህጻን እያለች የጀመራት የጭንቅላት በሽታም እስካሁን መፍትሔ አላገኘም፡፡

1060
0

ጭንቅላትዋ ላይ ያለውን ፈሳሽ በሽንት መልክ እንዲወገድ ቱቦ ተገጥሞላት  መሻሻል አሳይታ የነበረች ቢሆንም አሁን ግን በከበባው ምክንያት ምንም አይነት ህክምና ማግኘት እንዳልቻለች የምትገልጸው ታዳጊዋ፤ በሽታውን ተቋቁሜ እንዳልኖር አዳጋች የሆነብኝ ጊዜ የማይሰጠው ርሃቡን ነው፤ በጣም ርቦኛል እንጀራ እፈልጋለሁ ግን የሚላስ የሚቀመስ የለም፤ አብዛኛውን ጊዜ ሳልበላ ነው የምውለው ትላለች፡፡ ይህን ሁሉ ችግር ተቋቁማ በመኖርና ባለመኖር መካከል ሆና እየታገለች ያለችው ታዳጊ  ኤደን ገብረመድህን፤  እድሜዬ በጨመርኩ ቁጥር እናቴን እያዳከምኳት ነው፤ በርሃብ ውስጥ ሆና እኔን ለመሸከምም አስቸጋሪ ነው፤ ስለዚህ በራሴ እንቀሳቀስ ዘንድ የዊልቼርና  የህክምና ድጋፍ እሻለሁ ትላለች፡፡

ድጋፍ ተደርጎልኝ ከዚህ በሽታ ድኜ ትምህርቴን መጨረስ እፈልጋለሁ፤ የምትለው ታዳጊ ኤደን እንደ እኔ በበሽታ የሚሰቃዩትን ለማከም ዶክተር የመሆን ህልም አለኝ ትላለች፡፡

የኤደን እናት ወይዘሮ ሄዋን ዘውደ በሽታውና ርሃቡ ተደማመሮ የጨለማ ህይወት እየመራሁ ነው ይላሉ፡፡

ጎረቤቶችዋ በበኩላቸው ህጻን ኤደን ህክምና አግኝታ የተሻለ ህይወት መኖር ሲገባት በከበባው ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆናለች ይላሉ፡፡

የኤደንን ጉዳይ እንደ አብነት አነሳን እንጂ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ በጣለው ከበባና ክልከላ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራዋይ ህይወት  እጣ ፋንታ እንዳደረገው የሚታወቅ ነው፡፡

መነሳትና መሄድ አትችልም በሽታውን እንዳይበቃት ደግሞ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ባለመኖሩ ህይወት ከባድ ሆነብናል፤ ወደ ትምህርት ቤት ራሴ ነኝ አዝዬ የማመላልሳት፤ እቤትም የሚያግዘኝ ስው ስለሌ የትም ቦታ ስሄድ ይዥት ነው የምዘሮው፡፡ ባለኝ አቅም ስራ ሰርቼ የእለት ምግባችንን እንዳላመጣ እንኳን የሚያይልኝ ሰው የለም፡፡ አባትዋም የለም ብቻዬን ነው የማሳድጋት፡፡ ስለዚህ የእራሴ እና የልጄ ህይወት  ከባድ ችግር ውስጥ ነው ያለነው ስራ አልሰራም ከልጄ ጋር እዚች ቤት እግሬ እና እጄ አጣምሬ ነው የምውለው፡፡

Previous articleየግንቦት 20 የድል በዓል የሚከበረው ኢትዮጵያ በአለም ማህበረ-ሰብ የልማት ማእከል በመባል ተፅእኖ ፈጣሪ እንድትሆን አድርጓታል፡፡
Next articleየአክሱም ሆስፒታል በመድሃኒትና የሕክምና ቁሰቁስ እጦት ምክንያት ግልጋሎት መስጠት ወደ ማይችልበት ሁኔታ መድረሱን ተነገረ፡፡