ራሱን የለውጥ ቡዱን እያለ የሚጠራው ፋሽስቱ የአብይ ቡዱን ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በማሰርና በማንገላታት በአገሪቷ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው የፕሬስ ነፃነት ቁልቁል እንዲወርድ እያደረገ መሆኑነ ሲፒጄይ ባወጣው መግለጫ አስረድቷል፡፡
የፋሽስት ቡዱኑ ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት እውነታን የሚዘግቡ ጋዜጠኞችን በማሰርና በማንገላታት በምስራቅ አፍሪካ ላሉት አገራት ኤርትራን ቀጥላ በቀዳሚነት የምትጠቀስ አገር አድርጓታል ብሏል የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ፡፡
አገሪቷ በጋዜጠኞች ዘገባ ላይ የቅድመ ምርመራ በማድረግ በእጅጉ ከሚያደርጉ አገራት ዋነኛዋ ሆናለች ያለው ዘገባው በተለይም የኢንቴርነት አገልግሎት በመዝጋትና የፀረ ሽብር አዋጅ የሚል ሰበብ በማውጣት አፈናና እስር እያካሄደች ትገኛለች ብሏል፡፡
በትግራይ እየተካሄደ ያለውን የጀኖሳይድ ጦርነት የፋሽስቱ ቡዱን አዛብቶ በማቅረብ መጠመዱን ተከትሎ በርካታ የመገናኛ ብዙሃን ቡዱኑ የተዛባና የተምታታ ሃሳብ እያቀረበ መሆኑን ባጋለጡበት ወቅት ወደ እስርና እንግልት እየተዳረጉ መሆናቸው ሲፒጄይ አስረድቷል፡፡
የፋሽስት ቡዱኑ በትግራይ ህዝብ ላይ የጀመረውን ጦርነት እውነታውን በሚዘግቡ ጋዜጠኞች ነፃና ገለልተኛ ሆነው ስለጦርነቱና እያስከተለ ስላለው ጉዳት ሲዘግቡ በፋሽስቱ ቡዱን ተላላኪዎች የማዋከብ፣ ማንገላታትና እስራትን ጨምሮ ለተለያዩ ጥቃቶች እየተዳረጉ ናቸው ብሏል፡፡
ጦርነቱን ተከትሎ አሚኒስት ኢንተርናሽናልና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የፋሽስቱ ቡዱን በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈፀማቸው አረጋግጠዋል ያለው የሲፒጄይ መግለጫ ይህም የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጭምር ያሉበት የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት መረጃ እንዳለውም አመልክቷል፡፡
ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 63 ጋዜጠኞችና የሚዲያ ባለሙያዎች በፋሽስቱ መታሰራቸው የዘገበው የጋዜጠኞች መብት ተከላካዩ ሲፒጄይ በዋነኛነት በአዲስ አበባ፣ በአሮሚያ፣ በአማራ፣ በዓፋርና በሶማሌ ክልሎች ተንቀሳቅሰው ይኖሩ የነበሩ ናቸው ብሏል፡፡
ፋሽስቱ ቡዱን በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በየጊዜው በሚያካሂደው የስልክና ሌላ መገናኛ መቋረጥ ተከትሎ የተሟላ መረጃ ሊገኝ አለመቻሉን በመግለፅ ሰፋ ያለ ጥናትና ምርምር ቢካሄድ ግን ቁጥሩ ከዚህ ሊበልጥ ይችላል ብሏል፡፡
ከታሰሩት ጋዜጠኞች አብዛኛዎቹ ወደ ፍርድ ቤት እንደማይቀርቡ የጠቀሰው ሲፒጄይ ወደ ፍርድ ቤት የቀረቡትም ምርመራቸው አልተጠናቀቀም የሚል ተመሳሳይ መልስ በማቅረብ ተደጋጋሚና አሰልቺ የጊዜ ቀጠሮ በመውሰድ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ጋዜጠኞቹና የሚዲያ ባለሙያዎቹ ይበልጥ እንዲሰቃዩ እያደረገ መሆኑን የጋዜጠኞች መብት ተከላካዩ አመልክቷል፡፡
አንዳንድ ጋዜጠኞችም በማይታወቅ ስፍራ እንደሚታሰሩ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውና የህግ ባለሙያዎች እንዳያገኙዋቸው እያደረገ መሆኑን የጠቀሰው ሲፒጄይ አንዳንዶቹም ማንነታቸው በማይታወቁ የፀጥታ ሃይሎች እየታፈኑ የሚወሰዱ መኖራቸው አስረድቷል፡፡
የትግራይ ቴሌቭዥኑ ጋዜጠኛ የነበረው ዳዊት ከበደና ሲሳይ ፊዳ የተባለው ጋዜጠኛ ከስራቸው ጋር በተያያዘ ጉዳይ በፌዴራል ባለስልጣናት መገደላቸው ያስታወሰው ሲፒጄይ የኒውዮርክ ታይምስና የዘ-ኢኮኖሚስት የተባሉት የውጭ ጋዜጠኞችም ከኢትዮጵያ እንዲባረሩ መደረጉን አመልክቷል፡፡
የፋሽስቱ አብይ ቡድንና በክልል የሚገኙ የቡድኑ ተባበሪ ባለስልጣናት ጋዜጠኞችን ከመግደል፣ ከማሰርና ከማንገላታት ሊቆጠቡ እንደሚገባና ጋዜጠኞች ከሚሰሩት ስራ ጋር በተያያዘ በሚደርስባቸው ተፅእኖ ምክንያት እየታየባቸው ካለው የፍርሃት ድባብና መሸማቀቅ እንዲወጡ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብሏል የጋዜጠኞች መብት ተከላካዩ ሲፒጄይ፡፡
እንዲሁም የፕሬስ ነፃነትን ካለመጋፋትና ጋዜጠኞችና የሚዲያ ባለሙያዎች እውነትን ፈልፍሎ ለማውጣት የሚያደርጉት ጥረት የቅርብ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ የፕረስ ነፃነትን ሊያጎለብቱ ይገባል ብሏል ሲፒጄይ፡፡
ተካ ጉጉሳ