Home ዜና የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልእክተኞች በትግራይ መሰረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች ባፋጣኝ እንዲጀመሩ...

የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልእክተኞች በትግራይ መሰረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች ባፋጣኝ እንዲጀመሩ ስምምነት ላይ መድረሳቸው አስታወቁ፡፡  

535
0

ማምሻውን ወደ አዲስ አበባ የተመለሱት የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኞች በትግራይ መሰረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች ባፋጣኝ እንዲጀመሩ ስምምነት ላይ መድረሳቸው አስታወቁ።

የአሜሪካና የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ  ልዩ መልእክተኞች ማይክ ሀመር እና አንቴ ዌበር ዛሬ ከትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር በሰላም ድርድሩ ዙሪያ ከተወያዩ በኋላ ማምሻውን ባወጡት የጋራ መግለጫ በትግራይ የታወጀውን ጦርነት እንዲያበቃና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ፖለቲካዊ ውይይት ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ መሠረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች ማለትም የኤሌክትሪክ፣ የባንክ፣ የቴሌኮሙኒኬሽንና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች ባፋጣኝ አገልግሎት እንዲጀምሩ ልዩ መልእክተኞቹ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ያመለከተው መግለጫው የትግራይ መንግስት መሠረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች ለማስጀመር ወደ ትግራይ ለሚሰማሩ ባለሙያዎች የድህንነት ዋስትና እንደሚሰጥ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብና የፋሽስቱ የአብይ ቡድን ማረጋገጣቸው የጋራ መግለጫው አስረድቷል።

ይህ የደህንነት የዋስትና ማረጋገጫ መሠረታዊ የህዝብ አገልግሎቶቹ ለማስጀመር   እንቅፋት እንደማይኖር መግለጫው አመልክቷል።

ከዚህ ባልተናነሰ መልኩ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለትግራይ ህዝብና የሌሎችም አጓራባች ህዝቦች ተደራሽ እንዲሆን፤ በትግራይ ላይ በነዳጅ ፣ በጥሬ ገንዘብና በማዳበርያ ላይ የተጣለው ክልከላ መነሣት እንዳለበት የአሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልእክተኞች የጋራ መግለጫ አስረድቷል።

የጋራ መግለጫው በመጨረሻ ዕርቀ ሰላም እንዲወርድ የተጠያቂነት ጉዳይ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አመልክቶ ዓለም አቀፉ አጣሪ ኮሚሽን ተአሚኒ ምርመራ ለማካሄድ እንዲችል በጦርነቱ በተጎዳው አካባቢ እንዲንቀሳቀስ የሁለቱም ወገኖች ትብብር እንደሚሻ አስገንዝቧል።

ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች ከጠብ አጫሪ ንግግሮችና አገላለፆች እንዲቆጠቡም አሳስቧል የጋራ መግለጫው ።  

Previous articleፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ የምግብና መድሃኒት ክልከላ እንደ ጦር መሳርያ በመጠቀም የጀኖሳይድ ጦርነቱን ቀጥሎበታል፡፡
Next articleየፋሽስቱ ቡዱን ከትግራይ ህዝብ ጋር እያካሄደ ያለውን ጦርነት ተከትሎ እውነታውን ለመዘገብ የሚሞክሩ ጋዜጠኞችን እያፈነ በመሆኑ አገሪቷ በፕሬስ ነፃነት ላይ እያሳቸው  ያለውን  አፈና በከፍተኛ ሁኔታ ላይ ተባብሶ መቀጠሉን የአለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተከላካይ /ሲፒጄይ/ ገለፀ፡፡