Home ዜና የፋሽስቱ የአብይ ቡድን ሰራዊት በምስራቅ ሸዋ ዞን በቦሰት ወረዳ በህጻናት ላይ ግድያና...

የፋሽስቱ የአብይ ቡድን ሰራዊት በምስራቅ ሸዋ ዞን በቦሰት ወረዳ በህጻናት ላይ ግድያና አፈና አካሄደ።

1082

እንደ OMN ዘገባ በስፍራው ከብት በማገድ ላይ ከነበሩት ህፃናት መካከል አንድ ሲገደል ሌሎቹ ሶስት ህፃናት ታፍነው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል ብሏል፡፡

የልጆቻቸውን መጥፋት ለፖሊስ ጣብያ ያመለከቱ ወላጆችም የልጆቻቸው አስከሬን ጫካ ሄደው አንዲፈልጉ የተነገራቸው ሲሆን  የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያለበት ቦታ የምታሳዩን እናንተ ናቹህ በማለት በማያቁት ጉዳይ ላይ እንግልት እንደደረሰባቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡

የፋሽስቱ ሰራዊት በገባባቸው የኦሮምያ አካባቢዎች  ከብት የሚጠብቁ አረኞችን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያለበት ቦታ አሳዩን በሚል ሰበብ ንፁሃንን እያሰቃዩና እየገደሉ መሆናቸው OMN በዘገባው አመላክቷል፡፡

ፋሽሽቱ የአብይ ቡድን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ለማጥፋት በሚል ሰበብ ባወጀው የፀረ ሽምቅ ዘመቻ በድሮንና በሄሊኮፕተር የታገዘ ጥቃት በማካሄዱ ንፁሃንን ለሞት እና ለስደት በመዳረግ ላይ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል።