Home ዜና የ2021 የአለም የእርሻ ሽልማት የሎሬትነት ማእረግን፤ ሎሬት ፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለ በመቐለ  እውቅና...

የ2021 የአለም የእርሻ ሽልማት የሎሬትነት ማእረግን፤ ሎሬት ፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለ በመቐለ  እውቅና አሰጣጥ መድረክ ተከናወነ፡፡

1063

የ2021 የአለም የእርሻ ሽልማት የሎሬትነት ማእረግን የተጎናፀፉት ሎሬት ፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለ ያገኙት እውቅና ለበለጠ ስራ እንደሚያነሳሳቸው እና  በጦርነቱ የተጎዳው የትግራይ እርሻ ልማት ዘርፍ ለመመለስ ከፍተኛ ስራዎችን እያከናወኑ መሆናቸው ተናገሩ፡፡

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ገና ከጀምሩ 30 ተማሪዎችን ይዞ በሞሞና ዛፍ ጥላ ስር ሲመሰረት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት  በመሆን ዩኒቨርሲቲው አሁን ላለበት እድገት እንዲደርስ መሰረት ጥለዋል፡፡

 ከዚያ በተጨማሪም በእርሻ ልማት ዙርያ ምርምሮችን በመስራት አመርቂ ውጤት እንዲመዘገብ አስችለዋል፣ በዚህ ተግባራቸውም 2021 የአለም የእርሻ ሽልማት የሎሬትነት ማእረግን እንዲጎናፀፉ ሆነዋል ሎሬት ፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለ፡፡

ሎሬት ፕሮፌሰር ምትኩ በትግራይ በተጣለው ከበባና ክልከላ ምክንያት ወደ ቦታው አቅንተው ሽልማታቸውን መቀበል ባይችሉም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት የምስጋናና እውቅና አሰጣጥ መድረክ የተዘጋጀላቸው ሲሆን በመድረኩም የተሰጣቸው ሽልማት የበለጠ እንዲሰሩ የሚያነሳሳቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ሎሬት ፕሮፌሰር ምትኩ ሀይለ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በቆዩባቸው የአመራር አመታትና በእርሻ ልማት ዙርያ ምርምሮችን በመስራት አርአያ የሆኑ ናቸው ሲሉ የቀድሞ ተማሪዎቻቸውና የስራ ባልደረቦቻቸው ምስክርነታቸው ይሰጣሉ፡፡

ለዚህ ድልና ስኬት ያበቃቸው በዋናነት ለህዝባቸው ያላቸው ቁርጠኝነትና የማገልገል መንፈስ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

አሁን ያገኙት እውቅና ለበለጠ ስራ የሚያነሳሳቸው መሆኑን የገለፁት ሎሬት ፕሮፌሰር ምትኩ ሀይለ በቀጣይም በጦርነቱ የተጎዳው የእርሻ ልማት ዘርፍ ለመመለስ ከፍተኛ ስራዎችን እያከናወኑ መሆናቸው ተናግረዋል፡፡

ዊንታ ዘላለም