Home ጥዕና ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖም ሰብኣዊ እርዳታ በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ የአለም ማህበረሰብን ...

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖም ሰብኣዊ እርዳታ በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ የአለም ማህበረሰብን  አወገዙ፡፡

707
0

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖም  ዕርዳታ ለሚሹ ወገኖች የሚቀርበው ሰብኣዊ እርዳታ በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ የአለም ማህበረሰብን  አወገዙ፡፡

የአለም ማህበረሰብ  ትግራይን፣የመንን ፣አፍጋኒስታንን ሶርያንና የተቀረው  ዓለም ትኩረት ነፍጓቸዋል ያሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የአለም ማህበረሰብ ወደ ቀልቡ እንዲመለስና ሁሉንም በአንድ ዓይን እንደሚያይ ተስፋቸውን ገልፀዋል ፡፡

 “የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥቁሮችንና ነጮችን እኩል ያያል ወይ  አላውቅም  ነገርግን ባለፈው ሳምንት እንዳልነው የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የዩክሬንን  ለመርዳት የሚያደርገው ርብርብ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው ምክንያቱም ዳፋው  ለመላው አለም ላይ የሚተርፍ ነውና፡፡” 

ያሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡለትግራይ፣ የመን ፣አፍጋኒስታን፣ሶርያና ለተቀረው ዓለም ትኩረት ነፍጓቸዋል በማለት የዩክሬንን ያህል ይቅርና የእርዳታውን ሽርፍራፊ እንኳን እየደረሳቸው አይደለም በማለት ኢፍትሃዊነቱን አጋልጠዋል፡፡

ዓለም ሁሉንም ነጩንም ጥቁሩን የሰው ዘር በእኩል ዓይን እያስተናገደች ነው ለማለት እንደሚቸገሩ ያመለከቱት ዶ/ር ቴዎድሮስ በጆርጅ ኦርዌል  አኒማል ፋርም በተሰኘ የልብ ወለድ  ነገር ግን የአለማችንን ኡነታን በሚያንጸባርቀው መጽሀፍ  የሰፈረውን ሁሉም እንስሳት እኩል ናቸው አንዳንድ እንስሳት ግን የበለጠ እኩል ናቸው የሚለውን አባባል በመጠቀም  ዓለም በሰው ዘር ላይ የምታሳየውን አድልዎ  ነቅፈዋል፡፡

 በዚህ ጉዳይ ላይ ግልፅና ቀጥተኛ መሆን አለብኝ ዓለም የሰው ዘርን ሁሉ በእኩል ዓይን እያስተናገደች አይደለችም አንዳንዶች ከሌሎች የበለጠ እኩል ናቸው ይህንን  ስናገር ያመኛል ነገር ግን የማየው ይህንኑ ኡውነታ ነውና ለመቀበል ያስቸግረኛል::

ዶ/ርቴዎድሮስ በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫቸው የአለም አቀፉ ማህበረሰብ  ወደ ቀልቡ ተመልሶ ሁሉንም የሰው ዘር በእኩል ዓይን እንደሚያስተናግድ ተስፋቸውን ገልፀዋል፡፡                            

የCBSዋ ጋዜጠኛ  ሰሞኑን ከሂዩማን ራይትስ ወች ባልደረባ በነበራት ቆይታ 6 ሳምንት ያስቆጠረው የዩክሬን ጦርነትና  ለ17 ወራት የዘለቀው የትግራይ ጦርነትን  በማነፃፀር የአለም አቀፉ ማህበረሰብ  በትግራይ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ላይ ያሳየው ትኩረት ለምን አናሳ ሆነ ብላ ጥያቄ አቅርባ  እንደነበር ይታወሳል፡፡

Previous articleየፀጥታው ምክርቤት በትግራይ ጉዳይ ላይ የሰብአዊ አቅርቦት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር  እንደሚመክር ተገለፀ፡፡
Next articleየአማራ ባለስልጠናት የትግራይ ተወላጆችን ከሰብአዊ እርዳታና ከመንግስታዊ አገልግሎት እንደከለከልዋቸውየዘገበው the Economist  የትግራይ ተወላጆች ያመረቱትና ለውጭ ገበያ የተዘጋጀን የትግራይ ባለሀብቶች የሰሊጥ ምርት የአማራ ተወላጆች እንዲዘርፉትና እንዲያጓጉዙት ፍቃድና ዋስትና እንደሰጡዋቸው አመላክቷል፡፡