—-
በፋሽስቱ የአብይ አህመድ ቡድንና ግብረ አበረቹ ከምእራብ ትግራይ ተፈናቅላ በዓዲግራት ከተማ የምትገኘዉ የ19 ዓመቷ ኤደን የማነ በመድሃኒትና በህክምና እጦት እየተሰቃየች ትገኛለች፡፡
ኤደን የማነ የ 19 ዓመት ሩጣ ያልጠገበችና ተጫዉታ ያልደከመች ህፃን ነች፤ ይህች ህፃን የአስረኛ ክፍል ትምህርቷ እየተከታተለች ለቀጣይ ለሚገጥማት ብሩህ ተስፋ እያሰበች በዓዲ ጎሹ ከተማ ትምህርቷ ትቀጥል ነበር፤ ከዛ በኋላ ግን የትግራይ ህዝብ ጠላቶች እግራቸዉ የትግራይ መሬትን እንደረገጡ በሰለማውያን ሰዎች ላይ የተለያዩ ግፎች ሲፈፅሙ የታዘበችዉ ትንሿ ኤደን ህይወትዋን ለማትረፍ ተወልዳ ካደገችበት ከምእራብ ትግራይ በመሸሽ ወደ በምብራቃዊ ዞን ዓዲግራት ከተማ ተጠልላለች፡፡
ከቤተሰቦቿ ጋር በፍቅር ትኖርበት በነበረዉ አከባቢ ብዙ መከራዎችን ካሳለፈች በኋላ እንደማንኛዉም ትግራዋይ በሰዉ ሰራሽ የርሃብ አለንጋ እየተሰቃየች ባለችበት ወቅት የስኳር በሽታ ህመም ተጠቂ እንደሆነች አወቀች፡፡
አሁን ላይ ህፃን ኤደን በምግብና በመድሃኒት እጦት በዓዲግራት ጠቅላላ ሆስፒታል በከባድ አደጋ ዉስጥ ሁና ቀናቶችን ያለ ምግብና መድሃኒት በስቃይ እያለፈችዉ ትገኛለች፡፡
የዓለም ማህበረ-ሰብ በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለዉ የጀኖሳይድ ወንጀል በመረዳት በተለየም ለህፃናትና በቆየ በሽታ ለሚሰቃዩ የማህበረ-ሰቡ አካላት ሊደርሱላቸዉ እንደሚገባ ህፃን ኤደን ትማፀናለች፡፡
ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ የምግብና መድሃኒት ክልከላ እንደ ጦር መሳርያ በመጠቀም ፣ ለዓለም ማህበረ-ሰብ ለማታለልና ጫናው ለማቅለል፣ የቶክስ ማቆም ውሳኔ እና የሰላም ስምምነት ሁኔታ በሌላ መልክ ከበባና ክልከላ በማጠናከር የጀኖሳይድ ጦርነቱን ቀጥሎበታል፡፡
ፍረወይኒ መንገሻ