Home ዜና ፋሽስት የአብይ ቡድን ለ2015 ዓ/ም በጀት አመት ያቀደውን ረቂቅ በጀት በቋፍ ያለውን...

ፋሽስት የአብይ ቡድን ለ2015 ዓ/ም በጀት አመት ያቀደውን ረቂቅ በጀት በቋፍ ያለውን ኢኮኖሚ በማባባስ  በአገሪቱ  ከፍተኛ የበጀት ጉድለት  ሊያስከትል እንደሚችል ተዘገበ፡፡

971

በትግራይ ጦርነት ኢኮኖሚዋ የተንኮታከተው ኢትዮጵያ አሁን ከመደበችው ከፍተኛ በጀት 60 በመቶ ለመከላከያና ለአስተዳዳራዊ አገልግሎት እንዲውል ማድረጉ ኢኮኖሚዋን የበለጠ እንዲያሽቆለቁል የሚያደርግ እንደሆነ ጠቁሟል ሪፖርተር ጋዜጣ ፡፡

ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት ባለ ሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አድናቆት ሲቸራት ቆይቷል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በተከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ ግን የአገሪቷን የኢኮኖሚ እድገት በአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም IMFለመተንበይ አስቸጋሪ እንደሆነበትም መግለጹ ይታወቃል፡፡

ፋሽስት የአብይ ቡድን ትግራይ ላይ በለኮሰው የጀኖሳይድ ጦርነት ምክንያት ኢኮኖሚዋ የተንኮታከተው ኢትዮጵያ ለ2015 ዓ/ም የበጀት አመት 786 ነጥብ 6 ቢልዮን ብር በጀት እንደሚመደብ በረቂቅ  የ2015 በጀት ተመልክቷል፡፡

የአንድ ሀገር አመታዊ በጀት እየጨመረ በሄደ ቁጥር የአገሪቱ የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ያደርገዋል ምክንያቱም ብር በብዛት ታትሞ ስለሚሰራጭ ስለሚባብሰው ነው ይላል ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ፡፡ 

አሁን ከተመደበው ከፍተኛ በጀት 60 በመቶ ለመከላከያና ለለአስተዳዳራዊ አገልግሎት እንዲውል መደረጉ ደግሞ የአገሪቷን ኢኮኖሚ የበለጠ ቀውስ ውስጥ እንደሚከተው የኢኮኖሚ ምሁራን ይናገራሉ፡፡

ከጠቅላላ በጀቱ 44 በመቶ የሚሆነው ለአስተዳደራዊ አገልግሎት የሚውል ሲሆን ይህ አምራች ያልሆነውን ዘርፍ የአገሪቷን ኢኮኖሚ መቀመቅ ውስጥ የሚከት እንደሆነ ነው   የሪፖርተር ዘገባ የሚያስረዳው፡፡

አገሪቷን የጦር አውድማ  እንድትሆን ያደረጋት ፋሸስቱ የአብይ ቡድን  በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አብዛኛውን የአገሪቱን በጀት ወደ መከላከያ በማዞር ለጦር መሳሪያ መግዣ በማዋል የትግራይን ህዝብ እጨፈጨፈ ነው፡፡

አሁንም ከጦርነት አዙሪት ያልወጣው ፋሽስቱ የአብይ ቡደን ለ2015  ከተያዘው አመታዊ በጀት አስራ አምስት በመቶ ለመከላከያ እንደሚመድብ በረቂቅ በጀቱ ተመልክቷል፡፡

 ይህ በኢህዴግ ዘመን ከነበረው ከአንድ በመቶ የማይበልጥ   የአገር መከላከያ አመታዊ በጀት ከፍተኛ እንደሆነ ዘገባው ያስረዳል ፡፡

ይህም የሚያመለክተው ፋሽስቱ ለመንገድ ግንባታ፣ ለትምህርት፣ ለመጠጥ ውሃና ለኢነርጂ ከመደበው በጀት በላይ ነው፡፡

የትግራይን ጨምሮ በመላ አገሪቱ እየተካሄዱ ያሉትን ጦርነቶች ከፍተኛውን የሀገሪቱ በጀት ወደ መከላከያ እንዲዛወር  አድርገውታል ይላል ዘገባው፡፡

ለመከላያ ከፍተኛ በጀት በመመደብ የሀገር ሰላም፣ ፀጥታ እና ደህንነት ማረጋገጥ አይቻልም ሲልም በሪፖርተር ድረ ገፅ የሰፈረው ዘገባ ያመለክታል፡፡

የጀኖሳይድ ጦርነቱ ባስከተለው አለም አቀፋዊ መገለልም  ሀገሪቱ ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማትና አበዳሪ አገሮች  ታገኝ የነበረውን አመታዊ የበጀትና የኢኮኖሚ ድጋፍ አሁን ማሽቆልቆሉ ያመለከተው የሪፖርተር ዘገባ፤

 አንድ የምጣኔ ሀብት ምሁር ጠቅሶ እንደዘገበው የኮሮና ወረርሽኝ፣ የዩክሬንና የሩስያ ጦርነት ጨምሮ በትግራይ በተካሄደው የጀኖሳይድ ጦርነት የአገሪቱን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ እንደተጎዳ አመላክቷል፡፡

ሁኔታች በዚህ ከቀጠሉም የኢኮኖሚ ድቀቱ ከዚህ በላይ ሊባባስ እንደሚችልም ነው ዘገባው ያመለከተው፡፡

ይብራህ እምባየ