Home ዜና የዓይኒ ዋሪ በአል ዝግጅት

የዓይኒ ዋሪ በአል ዝግጅት

317

የዓይኒ ዋሪ በአል ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቱ ጠብቆ በድምቀት ለማክበር አስፈላጊ ዝገጅት መደረጉን የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡በትግራይ ማዕከላዊ ዞን አክሱም ከተማ በየአመቱ ነሃሴ 24 ቀን በድምቀት የሚከበረውን የዓይኒ ዋሪ በአል ዘንድሮም በድምቀት ለማክበር አስፈላጊውን ዝግጅት መደረጉን የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ገብረመድህን ፍጹም ብርሃን ለትግራይ ቴሌቪዥን ገልጸዋል፡፡

በዓሉ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቱ ጠብቆ እንዲከበር ከርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተክርስትያን በጋራ እየተሰራ መሆኑን ነው ሃላፊው የገለጹት፡፡በትግራይ ታውጆ በነበረው የጀኖሳይድ ጦርነት ምክንያት ላለፉት ሶስት አመታት ያልተከበረው የአክሱም የዓይኒ ዋሪ በአል አሁን በተገኘው አንጸራዊ ሰላም በዓሉ ሲከበር በጦርነቱ ጾታዊ ጥቃትና ጉዳት የደረሰባቸው እና ከባድ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖች ፍትሕ እንዲያገኙ በማሰብ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

በአሉ በሰላም አንዲከበር አስፈላጊውን የጸጥታ ዝግጅት መደረጉን የገለጹት አቶ ገብረመድህን ከዛሬ ነሃሴ 21 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ የዓይኒ ዋሪ የቁንጅና ውድድር እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡በአክሱም ከተማ ነሃሴ 24 ቀን 2015 ዓ/ም በሚከበረው የዓይኒዋሪ በአል የበአሉ ታሪካዊ አመጣጥና ትውፊቱን የሚገልጹ የፓነል ውይይቶች እና በአሉን የሚያደምቁ የተለያዩ ትእይንቶች እንደሚካሄድም አቶ ገብረመድህን ተናግረዋል፡፡

በወልደሚካኤል ገብረመድህን