Home ዜና EU ኮሚሽን ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች ካላስጀመረ ምንም ዓይነት...

EU ኮሚሽን ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ የህዝብ መሰረታዊ አገልግሎቶች ካላስጀመረ ምንም ዓይነት የፋሽናንስ በጀት ድጋፍ እንደማያደርግ አስታወቀ።

532

POLETICO የተሰኘ ድረ ገፅ ሩስያ በአፍሪካ የምታራምደው ፖሊሲ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የያዙት አቋም ዳግም እንዲያስቡ ሊገደዱ ነው በሚል ርእሰ ባሳፈረው ፅሁፍ እንዳመለከተው ሞስኮ ከአፍሪካ ሃገራት ጋር ግንኙነት ለማጠናከር የትምወስደው እርምጃ የአውሮፓ ህብረት ሃገራት ፋሽስቱ የአብይ ቡድንን በጦር ወንጀለኝነት የሚከሰስ ቡድን ቢሆንም በሁኔታው በሩስያ እንቅስቃሴ ተገደው የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርጉለት ይችላሉ።

የኢንተናሽናል ክራለሲስ ግሩፕ ባልደረባ ዊልያም ዴቪድ ሰን በአውሮፓ ህብረት ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን ያለውን የሻከረ ግንኙነት ሩስያ ለራሷ ጥቅም እንዳታውለው በአውሮፓ ህብረት ሃገራት ዘንድ ፍርሃት ማሳደሩን ጠቁሟል።

የአውሮፓ ኮሚሽን በቅርቡ በሰብአዊነት የገንዘብ ድጋፍ ሥር  ለትምህርትና ጤና ፕሮጀክቶች የሚውል 81.5 ሚሊዮን ዩሮ እንዲመደብ ያዘዘ ቢሆንም ለፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የሚውለውን ገንዘብ ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን መዋቅሮች ውጭ እንደሚተገበር ግልፅ ማድረጉ የኮሚሽኑ ቃል አቀባይን ጠቅሶ Politico ዘግቧል።

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ላይ ባወጀው የጀኖሳይድ ጦርነት ምክንያት ሊያደርግ የነበረው የ1 ቢሊዮን ዩሮ የበጀት ድጋፍ ኮሚሽኑ ማቋረጡ ያስታወሰው Politico የአምባገነኑ የሻዕቢያ ሰራዊት ከትግራይ አስካለውጣና እና ቋሚ የተኩስ አቁም ውል እስካልተደረሰ ድረስ እንደማይለቀቅ ኮሚሽኑ ማስታወቁን ዘግቧል።

ፋሸስቱ የአብይ ቡድን ከትግራ መንግስት ጋር ለመነጋገር በሚመጣው ነሃሴ ወር ለድርድ ይቀመጣል የሚል  ጊዚያዊ የጊዜ ሰሌዳ መኖሩን ያመለከተው የፖለቲኮ ዘገባ ኮሚሽኑ በአገሪቱ ሁኔታውን ለማሻሻል  በፋሽስቱ የአብይ ቡድን በቂ ሥራ ተሠርቷል የሚል እምነት ባለመኖሩ የተቋረጠው የፋይናንስ በጀት ድጋፍ እንደማይለቅ አስታውቋል።

የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ በትግራይ በአስቸኳይ አገልግሎት መጀመር የነበረባቸው የባንክ ቴሌኮሚኒኬሽን ነዳጅ ኢነርጂ .ኮሚዩኒኬሽን የመሣሠሉ መሰረታዊ የህዝብ አገልግሎቶች ሥራ እስካልጀመሩ ድረስ ለፋሽስቱ ቡድን የፋይናንስ በጀት ድጋፍ አይደረግለትም ብሏል።

በቅርቡ ትግራይን ሌሎች አካባቢዎች መልሶ ለማቋቋም በሚል ምክንያት የዓለም ባንክ ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን የ300 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት መፈራረሙ ያመለከተው ፖለቲኮ ፋሎረንስ በሚገኘው የአውሮፓ ዩኒቨርስቲ ተቋም አስተማሪ የሆኑት የፓለቲካ ኢኮኖሚስቱ መሓሪ ታደለ ማሩ የዓለም ባንክ እርምጃ የተቻኮለና በአግባቡ ያልታሰበበት በማለት በማጣጣል ውሳኔው ጦርነቱን እንደመደገፍ ይቆጠራል ብለዋል።

ኩኖም ቀለሙ