Home ዜና እንግሊዝ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የአለም አቀፍ እንቅስቃሴዎች ለመከታተል ለአፍሪካ ቀንድ ቀይ ባህር...

እንግሊዝ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የአለም አቀፍ እንቅስቃሴዎች ለመከታተል ለአፍሪካ ቀንድ ቀይ ባህር አካባቢ ልዩ መልእክተኛ ሾመች።

630
0

እንግሊዝ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የአለም አቀፍ እንቅስቃሴዎች ለመከታተል ለአፍሪካ ቀንድ ቀይ ባህር አካባቢ ልዩ መልእክተኛ ሾመች።

——

የእንግሊዝ መንግስት በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የአለም አቀፍ እንቅስቃሴዎች ለመከታተል እና ሰብአዊ ቀውስን ለመፍታት በማለም ሳራህ ሞንትጉመሪ የአፍሪካ ቀንድና ቀይ ባህር አካባቢ ልዩ መልእክተኛ አድርጋ ሾማለች፡፡

ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት ሳራህ ሞንትጉመሪ ከዚህ በፊት በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እንግሊዝ ኤምባሲ የንግድና ኢኮኖሚ አማካሪ፤ በየመንና በኢራን ልዩ መልእክተኛ በመሆን እንዲሁም በኬንያ የእንግሊዝ ከፍተኛ ኮምሽን የልማት ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል፡፡

የአፍሪካ ተወካይ ቪኪ ፎርድ ሹመቱ በአፍሪካ ቀንድ ያለው የሰብአዊ ቀውስ ለመፍታት እና በቀይ ባህር አካባቢ ያለንን ግንኙነት ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል፡፡

ሳራህ ሞንትጉመሪ ከፍተኛ ዲፕሎማት በመሆናቸው ስራውን ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚያደርሱት አምናለሁ ሲሉም አስተያታቸውን ሰጥተዋል፡፡

አዲሷ ተሿሚ ሳራህ ሞንትጉመሪ በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ቀንድ በድርቅና በጦርነት ምክንያት ህዝቡ ለአስከፊ ችግር ተጋልጧል በማለት የዩክሬንና የሩስያ ጦርነት ባስከተለው አለም አቀፍ የምግብ እጥረትም የአካባቢው ህዝብ ለከፍተኛ ረሃብ እንዲጋለጥ አድርጓል ብለዋል፡፡

ስለሆነም በዚህ ወሳኝ ወቅት የአፍሪካ ቀንድና የቀይ ባህር አካባቢ ልዩ መልእክተኛ ሁኜ በመሾሜ ደስተኛ ነኝ ብለዋል፡፡

ዓለምአቀፍ ትኩረትን የሳበው የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባህር ቀጠና ከእንግሊዝ በተጨማሪ አሜሪካ በቅርቡ ደግሞ ቻይና ልዩ መልእክተኛ ከሾሙ ሃገራት መካከል ናቸው፡፡

Previous articleየኢሳያስ ወታደሮች በትግራይ ጀኖሳይድ ጦርነት ውስጥ  መሳተፋቸው  የተባበሩት መንግስታት  የሰብአዊ መብቶች ጉዳይ     አረጋገጠ ፡፡
Next articleበደቡብ ሱዳን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን  በተዘጋጀዉ መድረክ   ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ማንነት መሰረት ያደረግ ግፍ ተጋለጠ፡፡