Home ዜና በፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና በደቡብ ክልል የመንግስት ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት የበርካታ ሂወት...

በፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና በደቡብ ክልል የመንግስት ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት የበርካታ ሂወት መጥፋቱ ተገለፀ።

1062
0

—-

በሰሜን ኣሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማህበርና እንዲሁም የወላይታ ህብረት  በጋራ በመሆን ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት  የወላይታ ብሄር በኢትዮዽያ ታሪክና ሃገር ግንባታ ሂደት ከሌሎች የሃገሪቱ ህዝቦች በጋራ በመሆን ኢትዮዽያን በማልማትና ኣንድነቷና ልኣላዊነቷን በማስከበር ረገድ መስዋእትነት  እየከፈለ የኖረ ኩሩ ህዝብ መሆኑን በማውሳት በየዘመናቱ  የመጡ ገዥዎች  መዋቅራዊ በደልና ጭቆና ሲያፈራሩቁበት መኖራቸውን ባወጡት  የጋራ መግለጫ  ጠቁመዋል።

ለዓመታት የዘለቀው የራስን እድል በራስ የመወሰን የወላይታ ህዝብ ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጠው ኣሁንም በፋሽስቱ ስርዓት የክልል እንሁን ጥያቄ ኣጥብቃቹህ ለምን ትጠይቃላቹህ በሚል ምክንያት ብቻ በሶዶና በቦዲቲ ከተሞች በንፁሃን ዜጎች ላይ በፋሽስቱ ቡድን እና በደቡብ ክልል የመንግስት ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት የበርካታ ሂወት መጥፋቱ መግለጫው አመልክቷል።

የወላይታ ህዝብ እንደሌሎቹ የሃገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ሕገመንግስቱ ያጎናፀፈውን ራስን በራስ የማስተዳደር  ዲሞክራሲያዊ መብቱን  በማያዋላዳ ኣቋም ክልል የመሆን ጥያቄ ኣቅርቦ በዞኑ ምክር ቤት ኣስወስኖ  ጥያቄውን እስከ ፌዴሬሽን ምክርቤት በማቅረብ ውሳኔውን በመጠባበቅ ላይ እንደነበር የሚያስረዳው መግለጫው ይህንን ዲሞክራሲያዊና ሕገመንግስታዊ ጥያቄውን  ህዝቡ በሰለጠነና ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሲጠይቅ የነበረ ቢሆንም በፋሽስቱ ቡድን በኩል ምላሹ በተቃራኒው እና ሃይል  እንደነበረም መግለጫው ኣትቷል።

በሰሜን ኣሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማህበርና  በዋሽንግተን ዲሲ  ኣከባቢ የወላይታ ህብረት  በጋራ ባወጡት መግለጫም  የወላይታ ህዝብ በሌሎች ኣከባቢዎች እንደታየው  የሌላ ኣከባቢ ተወላጅን የገደለበት ፣ ያሸማቀቀበት  እንዲሁም ብሄር ለይቶ ያፈናቀለበትና ያሳደደበት ሁኔታ ኣለመፈጠሩን በመግለፅ  በኣሁኑ ግዜ  የወላይታን ህዝብ ፍላጎት  ወደ ጎን በመተው የፋሽስቱ ቡድን ካድሬዎች  በራሳቸው ውሳኔ ሰጭነት  ሕገ መንግስቱን በጣሰ አኳኃን ውሳኔ ለመስጠት  ለፌዴሬሽን ምክርቤት መቅረቡ  መግለጫው አክሏል።

 ይህ  ህዝቡን  ያፈነና የፋሽሰቱ  መንግስት ካድሬዎች እንጂ የህዝቡን ይሁንታ ያላገኘ ውሳኔ  ተመሳሳይ ስነልቦና ኣላቸው ከሚባሉት ህዝቦች ጋር ለመጨፍለቅ ብርቱ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ መግለጫው ጠቁሟል።

ይህ ኣፋኝ ውሳኔ የወላይታ ህዝብ መብትና ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም የአካባቢው  ህዝቦች ጥያቄና ፍላጎት የገፋ መሆኑን በመግለፅ  በሰሜን ን ኣሜሪካ የሚገኙ የወላይታ ተወላጆች ዲያስፖራ  ኣባላት የወላይታ ህዝብ ሕግና ስርዓትን ተከትሎ ያቀረበውን በክልል የመደራጀት ጥያቄ ለማዳፈን የሚደረገውን መንግስታዊ ኣፈና ተቀባይነት እንደለለው ባወጡት  ባለ 7 ነጥብ  የጋራ የኣቋም መግለጫ አስታውቀዋል።

Previous articleተቓውሞ ኦነግ ንመግለፂ ሕብረት ኣፍሪካ
Next articleየኦሮሞ ነፃነት ግንባር የአፍሪካ ህብረት በኦሮሚያ ያለውን ወታደራዊ ግጭት የብሄር ብጥብጥ ነው ብሎ መፈረጁን ወቀሱ።