34ኛው የትግራይ ዝክረ ሰማእታት ቀን በጨርጨር ነዋሪዎች ከትግራይ ሰራዊት ጋር በመሆን ሰማእታትን በሚዘክሩ ሁነቶች ተከብሮ ውሏል፡፡
——-
“ሰማእታትን በምንዘክርበት ወቅት የፈፀሙትና እየፈፀሙት ያለው ጀግንነት ከትውልድ ትውልድ ማስተላለፍ ይኖርብናል ም” ተብሏል ፡፡
በትግራይ ደቡባዊ ዞን የጨርጨር ወረዳ ነዋሪዎች ከትግራይ ሰራዊት ጋር በመሆን ለሰላሳ አራተኛ ጊዜ የዝክረ ሰማእታት ቀንን አክብረዋል ፡፡ በእለቱም ሰማእታትን የሚዘክሩ የተለያዩ መፈክሮች ተደምጠዋል ትርኢቶችም ቀርበዋል ፡፡
የትግራይ ደቡባዊ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቱ ኪሮስ ሰማእታትን በምንዘክርበት ወቅት በሰኔ ወር በኣሉላ ኣባ ነጋ የተሰየመው ዘመቻ ላይ የተገኘው ኣንፀባራቂ ድል ሰማእታትን በበለጠ የምንዘክርበትና ሰራዊታችን የፈፀመውና እየፈፀመ ያለውን ታላቅ ድል በመጠበቅ ህልውናችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል፡፡
ለትግራይ ህዝብ ህልውና መረጋገጥ ሲሉ አንድያ ህይወታቸውን የከፈሉና አሁንም የትግራይ ህዝብን ዘር ለማጥፋት የተዘጋጁትን ወራሪ ሃይሎች ለመደምሰስ የተከበረ መስዋእትነት እየከፈሉ ያሉ ጀግና የትግራይ ልጆች አላማ ለማሳካት የትግራይ ህዝብ አንድነቱን በበለጠ ማጠናከር ይገባዋል ሲሉም የጨርጨር ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ካልኣዩ ግደይ ገልፀዋል ፡፡
በዝክረ ሰማእታቱ የተገኙት የራያ ጨርጨር ወረዳ ነዋሪዎችና የጀግናው የትግራይ ሰራዊት ኣባላት በበኩላቸው በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀውን የጀኖሳይድ ወንጀል ለመመከት እየተደረገ ያለውን ህዝባዊ ትግል ከግብ ለማድረስ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመፈፀም ዝግጁ እንደሆኑ አረጋግጠዋል ፡፡
ፍሬሂወት ተ/መድህን