Home ዜና ላለፉት 30 ዓመታት የትግራይ ህዝብ በላቡና በጉልበቱ ያለማውን የደን ሀብቱን የፋሽስቱ ቡድን...

ላለፉት 30 ዓመታት የትግራይ ህዝብ በላቡና በጉልበቱ ያለማውን የደን ሀብቱን የፋሽስቱ ቡድን ና ግብረኣበሮቹ ኣስበውና ኣልመው በትግራይ ህዝብ ላይ በከፈቱት የጀኖሳይድ ጦርነት ምክንያት እንዲወድሙ  ሆነዋል ፡፡ ይሁንና  በትግራይ ህዝብ ጠላቶቸ የወደሙትን ደኖችና እጽዋቶችን ከክረምት መምጣት ጋር ተያይዞ  መልሶ ለማልማት በማቀድም  በክልሉ በተለያዩ ኣካባቢዎች የችግኝ ተከላ እየተከናወኑ የገኛሉ ፡፡

492

ጀግና የትግራይ ሰራዊትም በኣረንጓዴ ልማት ተጠቃሽ የነበረውን የትግራይ ደን  ወደነበረበት ለመመለስ በማቀድ ጠላትን እየመከትን እናለማለን እያለማን እንመክታለን በሚል መሪ ቃል በመቐለ የችግኝ ተከላ ኣካሂድዋል፡፡ በችግኝ ተከላው ላይ የተገኙት የትግራይ ሰራዊት ኣባላት ሰራዊቱ ጠላትን  በግንባር ከመደምሰስ ባሻገር ከ ህብረተሰቡ ጎን በመቆም በልማታዊ ተሳትፎ ላይ  የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል ፡፡

የትግራይ ህዝብ ተገዶ ያለፍላጎቱ ወደጦርነት ገባ እንጂ ፍላጎቱ ሰላምና ልማት መሆኑን የገለጹት ደግሞ የትግራይ ሰራዊት ኣመራር ኣባል የሆኑት ታጋይ ቀለም ገ/ስላሴ ሲሆኑ በፋሽስታዊያን የወደሙት የትግራይ የተፈጥሮ ሃብት ወደቀድሞ ለመመለስም ህዝቡና ሰራዊቱ በመተባበር ሊሰሩ እንደሚገባም ኣክለዋል ፡፡

በችግኝ ተከላው ወቅት የተገኙት ነዋሪዎች በበኩላቸው የትግራይ ሰራዊት የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እንዲሁም የትግራይ ልማትን ለማረጋገጥ እየፈጸመው ያለው ሁሉምአቀፍ ተሳትፎ የሚበረታታ መሆኑን በመግለጽ የተተከሉት ችግኞችን በተፈለገው መንገድ ግባቸውን እንዲመቱ   እንክብካቤ እንደሚያደርጉላቸው ቃል ገብተዋል ፡፡

በተመሳሳይ ትግራይን መልሶ ለማልማት ጠላትን እየመከትን እናለማለን እያለማን እንመክታለን በሚል መሪ ቃል  የዘንድሮው የችግኝ ተከላ በማይጨው ከተማ ተከናውንዋል ፡፡ የትግራይ ጠላቶች የትግራይ ህዝብን ለማጥፋት በፈጸሙት የጀኖሳይድ ወንጀል  ባልተናነሰ መልኩ ለ30 ኣመታት ያለማውን ደኖችና እፅዋቱ  ላይ  መፈፀሙንና ለዚህም ጀግናው የትግራይ ሰራዊት ከግንባር ባሻገር የወደሙትን ደኖች በማልማት የበኩሉን እያበረከተ መሆኑን ተገልፀዋል ፡፡