Home ዜና ፋሽስቱ የአብይ ቡድን የኢሳያስ ሰራዊት እንዲሁም የተስፋፊው የአማራ ሃይሎች በትግራይ ህዝብ ላይ...

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን የኢሳያስ ሰራዊት እንዲሁም የተስፋፊው የአማራ ሃይሎች በትግራይ ህዝብ ላይ የጀኖሳይድ ጦርነት ካወጁበት ጥቅምት 2013 ዓ.ም አንስቶ በትግራይ ህዝብ ላይ በርካታ ዘግናኝ ግፎች መፈፀማቸው ያስታውሰው የትግራይ ውጭ ግንኙነት ፅ/ቤት የተፈፀሙ ግፎች የሚያጣራ ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን እንዳይቋቋም ሲከላከሉ መቆየታቸው በአንፃሩ የትግራይ መንግስት ገለልተኛ መርማሪ አካል እንዲቋቋም በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱን ያትታል።

465
0

የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን አገልጋይና ተላላኪው የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጋራ ያካሄዱትና በብዙ እንከኖችን ጉድለቶች የተሞላው የምርመራ ውጤትን ተከትሎ የተመድ የሰብአዊ ም/ቤት ም/ቤት ባሰተላለፈው ውሳኔ መሠረት ዓለምአቀፍ ገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን መሰየሙ አስታውሷል መግለጫው

የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን በትግራይና በሌሎች አካባቢዎች የተፈፀሙ ግፎችን ተዓማኒና ገለልተኛ ምርመራ ያካሂዳል በሚል እሳቤ ሲቋቋም ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በኮሚሽኑ ላይ ንቀት ሲያሳይ የትግራይ መንግስት ግን የኮሚሽኑን ሥልጣንና ሕጋዊነትን መቀበሉ መግለጫው ያስታውሳል።

ይሁንና የኮሚሽኑ ተአማኒነትን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ምልክቶች በመታየታቸው የኮሚሽኑ ሥራ ለድርድር በመቅረቡ አደጋ ላይ መውደቁን ያትታል።

ለኮሚሽኑ ሥራ መቃናት መጀመሪያ ግልፀኝነት ውሳኝ መሆኑን ያመለከተው የትግራይ ውጭ ግንኙነት መግለጫ ምርመራወን በተመለከተ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ወቅታዊና በቂ መረጃ ማስተላለፉ ተአማኒ ምርመራ ለማካሄድ ጠቃሚ መሆኑን አመልክቷል መግለጫው

የጦር ወንጀሎችና በሰብአዊ ፍጡር ላይ የተፈፀሙ ግፎችን ለማጣራት ምርመራው  በተወሰነ መልኩ በምስጢር መያዙ አግባብነት ያለው ቢሆንም የምርመራውን ሂደት ለጉዳቱ  ሰለባዎች ሲሆን በምስጢር ለመደበቅ ለወንጀል ፈፃሚውን ሲሆን ግን በተለየ መልኩ ማስተናገድና ማባባል  እንደ አንድ በጣም አስፈላጊ ባለጉዳይ አድርጐ መመልከቱ በምርመራው ሂደትና ግኝቶች የኮሚሽኑ ሚዛናዊ ዳኝነትና ተአሚኒነት ላይ አደጋ የሚጥል እንደሆነ መግለጫው አስረድቷል።

ኮሚሽኑ የአዲስ አበባውን የ6 ቀን ቆይታ አጠናቆ ከተመለሰ በኃላ ባወጣው መግለጫ ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን ጋር ያካሄደው ውይይት ቀደም ሲል በጀኔቫ ያካሄደውን ውይይት ተቀጥያ መሆኑን ማመልከቱ ከወንጀል ፈፃሚው የፋሽስቱ ቡድን ቀጥታ የግንኙነት መስመር መክፈቱንና ለተበዳዩ የትግራይ ህዝብ ግን ጀሮ ደባ ልበስ ማለቱ በዳዮችን ተገቢውን ቅጣት እንደያገኙ ዋስትና የሚሰጥ እንደሆነም አስተውቋል።

ኮሚሽኑ ሆን ብሎ ከትግራይ መንግስት ጋር ትርጉም ያለው የግንኙነት መስመር ላለመፍጠር የሄደበት መንገድ የኮሚሽኑ ሚዛናዊ ዳኝነትን መስዋእት ለማድረግ መዘጋጅቱን ያመለክታል ብሏል መግለጫው

በጠቃላይ በዚሁ የምርመራ ማዕቀፍ ውስጥ ትግራይን እንደማይመለከት  ባለድርሻ አካል  አድርጎ  የሚያገል የሚያይ ማናቸውም ሙከራ የተሳሳተና ተቀባይነት እንደሌለው መግለጫው አስገንዝቧል።

የትግራይ መንግስት አሁንም ኮሚሽኑ በሂደት አሠራሩን ያስተካክላል ብሎ በጥብቅ እንደሚያምን የገለፀው መግለጫው ስፍር ቁጥር የሌላቸው የወራሪዎቹ የጀኖሳይድ ዘመቻ ሰለባዎች የተሟላ ፣ ተአማኒና ፣ ቀልጣፋ ፍትህ እንደሚሹ አመላክቷል።

ተበዳዮችን በመውቀስ የተጠመደውና ራሱን ከደሙ ንፁህ ለማድረግ የፍትህና የተጠያቂነት ጠበቃ አድርጐ በሚያየው የፋሽስቱ ቡድን የኮሚሽኑን ሥራ እንዲጠለፍ ሊፈቀድለት እንደማይገባም አሳስቧል መግለጫው

ኮሚሽኑ ለምርመራ ሥራው ያለምንም ጣልቃ ገብነት ግፎች ተፈፅምባቸዋል ተብለው በሚጠረጠሩ አካባቢዎች ያልተገደበ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ እንደፈቀድለት ከመጠየቅ ውጭ ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን ጋር ማናቸውም ግንኙነት ከማድረግ እንዲቆጠብ ያሳሰበው መግለጫው የፎረንሲክ ማስረጃን ጨምሮ ቁልፍ ማስረጃዎች ባግባቡ እንዲሰነዱ ማድረግ ለኮሚሽኑ ውጤታማ የምርመራ ሥራ ወሳኝ መሆናቸውን አመልክቷል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተመድ የሰበአዊ መብት ም/ቤት ባጠቃላይና የአጣሪ ኮሚሽኑ በተለይ የአማራው ተሰፋፊ ሃይል በምዕራብ ትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀሙት የትግራይን ተወላጆችን አፅም የማቃጠልና የጅምላ ጭፍጨፋዎችን ዘግናኝ ወንጀሎችን  በተመለከተ እንዳላዩና እንዳልሰሙ ሆነው ማለፋቸው ተስፋ አስቆራጭ ነው ያለው መግለጫው  ይህ የኮሚሽኑ ጀሮ ዳባ ልበስ ማለቱ በትግራይ ህዝብ ላይ እየቀጠለ ያለውን መሠረታዊ የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዲስፋፋ ምክንያት መሆኑን ጠቅሷል።

ከሁሉም የሚደንቀው ይላል የትግራይ ውጭ ግንኙነት መግለጫ ዜጎች በኢንተርኔት ማስረጃ የሚያቀርቡበት የሚያበቃበትን የጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱ ነው፣ በትግራይ ሁሉም የኮሙዩኒኬሽን አውታሮች በተዘጋጉበት ሁኔታ ይህ ማለቱ በትግራይ የደረሰው ግፍና ስቃይ መጠን አቃልሎ ማየቱን ያመላክታል ብሏል ።

መግለጫው አያይዞ ኮሚሽኑ ወንጀሉ በተፈፀመባቸው ቦታዎች እንዲንቀሳቀስ ዋስትና እንዲሰጠው ከመጠየቅ ይልቅ እንደሚፈቀድልን ተስፋ እናደርጋለን ብሎ መግለፁ ተገቢነት የሌለው አገላለፅ መሆኑን ገልጧል፡፡

 ያም ሆነ ይህ አሁንም የትግራይ መንግሥት ኮሚሽኑ ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆኑን አመልክቷል።

ኮሚሽኑ በሂደት አሠራሩን እንዲታረም ካላደረገና ለትብብር ብቻ ተብሎ የሚደረግን ትብብር ጊዜና ሃብት ከማባከን ውጭ ፋይዳ እንደሌለው በመገንዘብ ኮሚሽኑ የትግራይ ህዝብና መንግስት እንደባለጉዳዮች በምርመራው ሂደት ባግባቡ እንዲስተናገዱ ጠይቋል የትግራይ ውጭ ግንኙነት ፅ/ቤት      

Previous articleላለፉት 30 ዓመታት የትግራይ ህዝብ በላቡና በጉልበቱ ያለማውን የደን ሀብቱን የፋሽስቱ ቡድን ና ግብረኣበሮቹ ኣስበውና ኣልመው በትግራይ ህዝብ ላይ በከፈቱት የጀኖሳይድ ጦርነት ምክንያት እንዲወድሙ  ሆነዋል ፡፡ ይሁንና  በትግራይ ህዝብ ጠላቶቸ የወደሙትን ደኖችና እጽዋቶችን ከክረምት መምጣት ጋር ተያይዞ  መልሶ ለማልማት በማቀድም  በክልሉ በተለያዩ ኣካባቢዎች የችግኝ ተከላ እየተከናወኑ የገኛሉ ፡፡
Next articleየዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም ከካዛኪስታን ብሄራዊ የህክምና ሳይንስ ዩኒቨርስቲ የክብር የፕሮፌሰርነት ማአረግ ተበረከተላቸው፡፡