በላስቬጋስና አከባቢዋ የሚኖሩ የትግራይ ዲያስፖራ ማህበረ-ሰብ በዚሁ ሶስተኛ ዙር የመመከት እንቅስቃሴ በድጋሚ ታሪክ እየሰሩ እነደሚገኙም ተገልጿል፡፡
በተለያዩ የአለማችን ክፍል የሚገኙ የትግራይ ዲያስፖራ ማህበረ-ሰብ በከበባና በክልከላ ዉስጥ የሚገኘዉን ህዝባቸው ለማገዝ ባለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይን ህዝብ የትግል አንድ አካል በመሆን እያሳዩ ያሉትን እንቅስቃሴ አመርቂ ውጤት እያመጣ መሆኑን የተመለከተ ሲሆን የትግራይ ህዝብ ትግል በወሳኝ ምእራፍ ላይ በደረሰበት ባሁኑ ወቅትም ሶሰተኛዉ ዙር የመመከት ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉ ታውቋል፡፡

የትግራይን ህዝብ ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስፈልገዉን ሁሉ እገዛ ለማድረገ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረኮች የማካሄዱ ስራ ተጠናከሮ ቀጥሏል፡፡
በሁሉም ምእራፎች ደማቅ እንቅስቃሴና ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቁት በላስቬጋስ የሚኖሩ የትግራይ ዲያስፖራዎቸ አሁንም 357,000 ዶላር እርዳታ በመለገስ ድሉን ከጫፍ ለማድረስ አስተዋፆ እያደረጉ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ፍረወይኒ መንገሻ