——-
እናቱ በርሃብ ምክንያት በሞት የተለየችው የአርባ ቀናት እድሜ ያለውን ህፃን በበኩሉ በምግብ እጦት ሳብያ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እንደሚገኝ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ የቤተሰብ አባላት ገልፀዋል፡፡
በዓዲግራት ከተማ እስከ መጋቢት ወር 2014 ዓ/ም በርሃብና በመድሃኒት እጦት ምክንያት የበርካታ ሰዎች ህይዎት ማለፉን የከተማዋ የሰራተኞች ጉዳይና የህብረተ-ሰብ ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ዘርፍ ፅህፈት ቤት አስታውቋል ፡፡
ወ/ሮ ፀጋና ወ/ሮ ስእላ ፋሽስታውያን ወራሪ ሃይሎች በትግራይ ህዝብ ላይ ካወጁት የጀኖሳይድ ጦርነት ለማምለጥ ከሑመራ እና ዛላንበሳ ከተሞች ወደ ዓዲግራት ከተማ ተፈናቅለው በተፈናቃዮች ጊዚያዊ መጠለያ ጣብያ ላይ ነበር የተዋወቁት፡፡
ወ/ሮ ስእላ እንደሚገልፁት በወቅቱ ነብሰ ጡር የነበረች ወ/ሮ ፀጋን ዘመዳቸው መጠልያ ይሆናቸው ወደ ሰጧቸው የመኖረያ ቤት ወስደው አዋልደዋታል፡፡ ሆኖም ለአራስ የሚዘጋጅ ምግብ ይቅርና ለአንድ ለሊት የሚሆን የሚላስ የሚቀመስ ምግብ ባለ መኖሩ በርሃብ ምክንያት የወ/ሮ ፀጋ ህይወት እንዳለፈ ይናገራሉ ፡፡
የወ/ሮ ፀጋ ባለቤት አቶ ደስታ ግርማይ ፋሽስታዊያን በፈጠሩት ሰው ሰራሽ ርሃብ ምክንያት ባለቤቱ የ 40 ቀን እድሜ ያለው ጨቅላ ትታ ህይዎትዋ በማለፉ በችግር ላይ ችግር ተደራርቦበት ሊሸከመው የማይችለውን ከባድ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ይናገራል፡፡
ወ/ሮ ፀጋ ፋሽስታዊያን በፈጠሩት ሰው ሰራሽ ርሃብ ምክንያት ገና አይታ ያልጠገበችውን የ40 ቀን ህፃን ትታ ህይወትዋ እንዳለፈ የምትገልፀው የወ/ሮ ፀጋ ጓደኛ የሆነችው ሃረግ ህፃኑ በአሁኑ ወቅት ወ/ሮ ስእላ እጅ ላይ ቢሆንም ለህፃኑ የሚሆን ምግብ ግን ማግኘት እንዳልቻሉ ትግልፃለች፡፡
ፍሬሂወት ተ/መድህን