Home ዜና ኢትዮጵያ በትግራይ ለተፈጸመው ጀኖሳይድ ማስረጃ የማጥፋት ዘመቻ

ኢትዮጵያ በትግራይ ለተፈጸመው ጀኖሳይድ ማስረጃ የማጥፋት ዘመቻ

1394

ኢትዮጵያ በትግራይ ለተፈጸመው ጀኖሳይድ አጣሪ ቡድን እንዳይቋቋም እና የተባበሩት መንግስታት ላቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን በጀት እንዳይመደብለት ያቀረበችው ጥያቄ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ከምእራብ ትግራይ አስክሬን የማሸሽ ስራ እየሰራች መሆንዋን Globnewsnet ዘገበ፡፡

በምእራብ ትግራይ በግፍ የተረሸኑ የተጋሩ አስክሬን ገለልተኛ አካል መጥቶ ከማየቱ በፊት የፋሽስቱ ቡድንና እና የአማራ ተስፋፊ ሐይሎች በጋራ ማስረጃን የማጥፋት ስራ እየሰሩ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

ከአንድ አመት በፊት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የአምባገነኑ ኢሳያስ ወታደሮችና የአማራ ተስፋፊ ሀይሎች በምእራብ ትግራይ በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ የዘር ማጽዳት ወንጀል ስለመፈጸማቸውና ወንጀሉን በገለልተኛ አካል መጣራት እንዳለበት ገልጾዉ ነበር፡፡

አንቶኒ ብሊንከን ይህን ካሉ ከአንድ አመት በኋላ ኢትዮጵያ በትግራይ ለተፈጸመው ጀኖሳይድ አጣሪ ቡድን እንዳይቋቋም እና የተባበሩት መንግስታት ላቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን በጀት እንዳይመደብለት ያቀረበችው ጥያቄ በአብላጫ ድምጽ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ የፋሽስቱ ቡድንና የአማራ ተስፋፊ ሀይሎች በምእራብ ትግራይ በግፍ የተገደሉ የተጋሩ አስክሬን እያጓጓዙ መሆናቸውን Globnewsnet በድር ገጹ አስነብቧል፡፡

ባለፉት አስራ ስምንት ወራት በሺዎች የሚቆጠሩ በምእራብ ትግራይ ይኖሩ በነበሩ የትግራይ ተወላጆች በፋሽስቱ ቡድን፣ በአማራ ተስፋፊ ሀይል፣ በአምባገነኑ ኢሳያስ እና በሶማልያ ቅጥረኛ ወታደሮች ተረሽነዋል፡፡

እነዚህ በግፍ የተረሸኑ የተጋሩ አስክሬን ገለልተኛ አካል መጥቶ ከማየቱ በፊት መረጃን የማጥፋት ስራ እየሰሩ ነው ብሏል GNN በዘገባው፡፡  

በዚህ አስክሬን በማሸሽ ረገድ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ተባባሪ መሆኑን ተገልጿል፡፡

መረጃውን በማጥፋት እና እውነታውን እንዳይታወቅ በማዛባት እየሰሩ ያሉት የፋሽስቱ ቡድንና የአማራ ተስፋፊ ሚድያዎች በምእራብ ትግራይ የአማራ ተወላጆች በትግራይ ሰራዊት ከ1975 ዓ/ም ጀምሮ የተገደሉ ናቸው በሚል ተልካሻ ምክንያት ለወንጀላቸው ሽፋን  የጅምላ መቃብሮቹን እየቆፈሩ አስክሬኑን ወደ አማራ ክልል እየወሰዱት ነው ብሏል Globnewsnet በዘገባው፡፡  

ይህም የተባበሩት መንግስታት ስራውን ከመጀመሩ በፊት መረጃውን የማጥፋት ስራ እየሰሩ አንደሆነ ነው ዘገባው ያመለከተው፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት በሚል  በትግራይ ጀኖሳይድ የተሳተፉ፣ የጦር መሳሪያ ያቀረቡ፣ ስልጠና የሰጡ እና በገንዘብ የደገፉ አካላትን ተጠያቄ የሚያደርግ S3199 ውሳኔ ለአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት  እንደመራው ይታወሳል፡፡

ይብራህ እምባየ