ሰሞኑ፣ በኣፋር ምድር የተገኘው፣ የትግራይ ተወላጅ ንፁሃን ወገኖች፣ የጅምላ መቃብር፣ ዋነኛ ተጠያቂዎች፣ ኣረመኔዎቹ የፋሽስት ኣብዪ ኣህመድ ቡድንና ሸሪኮቹ ናቸው!! ሰሞኑ፣ ስታይ የሰነበተው፣ የትግራይ ተወላጅ ንፁሃን ወገኖች፣ የጅምላ መቃብር፣ ሆነው፣ በተለያዩ የኣፋር ቦታዎች ያሉት ሁሉም መቃብሮች፣ ዋነኛ ተጠያቂዎች፣ ትግራይን ከዓለም ካርታ፣ የትግራይ ህዝብን ደግሞ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት፣ ጆኖሳይድ ጭምር፣ በዓለም ኣቀፍ ፍርድቤት የሚያስከስሱ፣ ሁሉም ዓይነት ወንጀሎች፣ በህዝባችን እንዲፈፀም ወስነው፣ ያቀዱ፣ የመሩና ቅጥረኛ ኣራዊት ታጣቂ ሃይላቸውን ያሰማሩ፣ ኣረመኔው የኤርትራ ኣምባገነን መንግስት፣ የፋሽስት ኣብዪ ኣህመድ ቡድን፣ የኣማራ ተስፋፊ ሊሂቅና ኣመራር፣ እንዲሁም በእነዚህ ኣረመኔዎች ሳምባ የሚተነፍስ፣ በኣወል ኣርባ የሚመራው ምስለኔው የኣፋር ክልል ኣመራር ናቸው።
በዚህ ኣጋጣሚ፣ የሁሉም ኣረመኔ ወራሪዎች ሴራ፣ ማለትም፣ በትግራይ ህዝብ ላይ ያካሄዱትና እያካሄዱት ያለውን፣ ባርባራዊ የጀኖሳይድ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ የኣፋርና የትግራይ ህዝቦችን፣ መቆምያ ወደሌለው የማያባራ ጦርነት እንደሚደረግ ተረድታችሁ፣ ከጅምሩ የተቃወማችሁና ኣስከፊውና ዘግናኙ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ተከታትላችሁ፣ ትክክለኛ ኢንፎርሞሽን በመስጠት ያጋለጣችሁ የኣፋር የጎሳ መሪዎች፣ እንዲሁም ብዙሃኑ የኣፋር ተወላጆች ላደረጋችሁት ትግልና ላበረከታችሁት ኣስተዋፅኦ፣ የትግራይ መንግስት ያለውን ኣክብሮት፣ በትግራይ ህዝብ ስም ምስጋናውን ያቀርባል። ነገር ግን እጃቸውን በደም የተነከረው፣ የሁሉም ወራሪ ኣራዊት ታጣቂዎች፣ እንዲሁም፣ በኣወል ኣርባ የሚመራው፣ የኣፋር ክልል ኣመራር፣ የትግራይ ተወላጅ ንፁሃን ወገኖች በጅምላ የጨፈጨፈው፣ ቅጥረኛ ታጣቂ ሃይላቸው፣ የግዜ ጉዳይ ካልሆነ የማታ ማታ፣ የእጃቸውን እንደሚያገኙ ወዳጅም ጠላትም ሊያውቅ ይገባል።
ባለፉት ቀናት የታየው፣ የትግራይ ተወላጅ ንፁሃን ወገኖች፣ የጅምላ መቃብር፣ ባለፈው ዓመታት፣ የሳወዲ አረብያ መንግስት፣ በአስገዳጅ ወደ ኢትዮጵያ ያባረራቻው የትግራይ ተወላጆች፣ ከታጎሩባቸው ማጎርያዎች፣ እትብታቸው ወደተቀበረበት የትግራይ ምድር፣ በእግር ጨምሮ በተለያዩ የመጓጓዣ ኣማራጮች፣ ኣፋር ክልል እንደደረሱ፣ የኣፋር ህዝብ በጉልበት እየገዛ ያለው የኣወል ኣርባ ኣመራር ታጥቂ ሃይል፣ ወገኖቻችን በመያዝ፣ በሰመራና በሌሎችም ቦታዎቸ ኣጉራቸው የነበሩት እንዲሁም ዘንድሮ ከኣብዓላ( ሽኸት) ኣፍኖ የወሰዳቸው በገንዘባቸው፣ ጉልበታችውና፣ ዕወቀታቸው ጥረው ግረው ከመኖር የዘለለ ኣንዳችም እንከን ሳይነራቸው ማንነታቸው፣ እንደሃጥያት ተቆጥሮ፣ በግፍ ተጨፍጭፈው ያለፉ ንፁሃን የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ይህ ሰሞኑ የታየው፣ የትግራይ ተወላጅ ንፁሃን፣ የጅምላ መቃብር፣ ወራሪዎች፣ ከኣራት ዓመታት፣ በፊት፣ ያወጁት የሰነ-ልቦና ጦርነት በኣጠቃላይ፣ በዋነኝነት በለፉት 21 ወራት ያካሄዱትና ያካሄዱት ያለውን፣ የጆኖሳይድ ግልፅ የወታደራዊ ወረራ ጦርነት ኣካል ነው።
በመሆኑም፣ የወራሪዎቹ ጋሻ ኣጃግሬ የሆነው የኣወል ኣርባ ጨካኝ ኣመራር፣ የትግራይና የኣፋር ህዝቦችን ደም ለማቃባት፣ በትግራይ ተወላጅ ንፁሃን ወገኖች፣ ትንኮሳ፣ እስር፣ ማንገላታትና መግደል፣ የጀመረው 2012 ዓ/ም ነበር። የወራሪዎቹ ምስለኔው የኣወል ኣርባ ኣመራር፣ ይህንን እኩይ ተግባር ኣስቦ እና አቅዶ፣ ያካየደው በዋነኝነት፣ ከትግራይ በሚዋሰኑት የአፋር ከተሞች የሚነረው የኣፋር ህዝብ በሁለንተናዊ ትስስር የተጋመደውን፣ የትግራይ ህዝብ ጋር ለማጋጨት ነበር። ይኸውም፣ የኣወል ኣርባ አመራር በተለያዩ የኣፋር ከተሞች የሚኖረውን የትግራይ ተወላጅ እንዲፈናቀል፣ ላቡን አንጠፍጥፎ ለዓመታት ያፈራው ሃብት ንብረቱ ወረው፣ ባዶ እጁ ከአፋር እንዲባረር አድርጓል። ባጭሩ በኣፋር የተለያዩ ከተሞች፣ ለረዥም ዓመታት፣ ከኣፋር ህዝብ ጋር ተስማምቶ፣ በሰላም ሲኖር የነበረውን የትግራይ ተወላጅ፣ የኣወል ኣርባ ኣመራር በማፈናቀል፣ ሃብት ንብረት መውረርና መባረር ብቻ ኣላበቃም።
በመቶዎች የሚቆጠሩት ንፁሃን የትግራይ ተወላጆች፣ በወራሪ ሃይሎች ታጣቂዎች፣ በኣጠቃላይ በዋነኛነት በኣረመኔው የኢሳያስ ኣፈወርቂ መንግስት፣ ኣራዊት ታጣቂና፣ የኣወል ኣርባ ምንደኛ ቅጥረኛ ታጣቂ፣ በተለያዩ የኣፋር ቦታዎች በግፍ መገደላቸውን፣ የኣፋር ጨካኝ ኣመራር፣ ሴራና የጥፋት እከይ ተግባር የሚያውቁ የኣፋር የጎሳ መሪዎችና ንፁሃን የኣፋር ተወላጆች ያረጋገጡት ሃቅ ነው። ሆኖም በኣሁኑ ወቅትም፣ ከዘግናኝ የጀምላ እልቂት፣ በኣጋጣሚ የተረፉ፣ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ፣ ንፁሃን የትግራይ ተወላጆች፣ ሰመራ ከተማን ጨምሮ ከ40 ዲግሪ ሴንትግሬድ በላይ ሙቀት፣ ባላቸው የተለያዩ የኣፋር በረሃዎች፣ ታሽገው፣ በበሽታ እየተሰቃዩና በረሃብ እየተቀሉ፣ እንደቅጠል በመርገፍ ላይ ናቸው። የፋሽስት ኣብዪ ኣህመድ ቡድን፣ በኣሻንጉሊቱ፣ ኣወል ኣርባ፣ ከታሰሩት ንፁሃን የትግራይ ተወላጆች መካከል፣ ወጣቶች ለይቶ፣ ወደኣልታወቀ ስፍራ ወስዳቸዋል። በኣሁኑ ወቅት እነዚህ ንፁሃን ወገኖች፣ የት እንዳሉ በውል ኣልታወቀም።
ከእነዚህ ወጣቶችም፣ ከፊሉ ጨፍጭፎ እንደገደላቸው ተጨባጭ መረጃዎች ተገኝቷል። በመጨረሻም ሰሞኑ በኣፋር ምድር የተገኘው፣ የትግራይ ተወላጅ ንፁሃን ወገኖች የጅምላ መቃብር፣ ዋነኛ ተጠያቂዎቹ፣ ኣረመኔዎቹ የፋሽስት ኣብዪ ኣህመድ ቡድንና ሸሪኮቹ ናቸው። በመሆኑም፣ የዓለም ኣቀፍ ማህበረሰብ፣ ባለፉት ዓመታት፣ በማንነታቸው ብቻ፣ የታሰሩት ከ17 ሺ በላይ የቀድሞ የኢፈድሪ መከላከያ ሰራዊት ኣባላት ጨምሮ በሁሉም የኢ/ያ ኣካባቢዎች፣ በሆለከስት መልክ በኣስከፊው ማጎርያ ካምፖች ታጉረው የታሰሩት በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ንፁሃን ወገኖች በኣጠቃላይ፣ በተለይም እያገባደድነው ባለነው ዓመት ከተለያዩ የኣፋር ከተሞች ተለቅመው የቁም ስቃይ እያዩት ያሉት፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ፣ ሳይውል ሳያድር ከእስር እንዲለቀቁ፣ ህጋዊ ሃላፍነቱና ሞራላዊ ግዴታው ሊወጣ ይገባል። ከዚሁ በተጨማሪም በኣፋር ምድር በሁሉም ወራሪዎች፣ በትግራይ ተወላጅ ንፁሃን ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውና በመፈፀም ላይ ያለውን ጆኖሳይድ፣ በገለልተኛ ኣካል እንዲጣራ፣ የዓለም ኣቀፉ ማህበረሰብ ኣስፈላጊውን ሁሉን እንዲያደርግ የትግራይ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።
ዘላለማዊ ክብር፣ በጀኖሳይድ የጅምላ ጭፍጨፋ ላለቁ፣ ንፁሃን የትግራይ ተወላጆች!! ለዘመናት ተገምዶ የኖረው፣ የኣፋርና የትግራይ ህዝቦች፣ ግንኙነት በወራሪዎች ሴራ ኣይሸረሸርም!!ህልውናችንና ድህንነታችን በፈርጣማው ክንዳችን!!ትግራይ ታቸንፋላች!!የትግራይ መንግስትሓምሌ 19/2014 ዓ/ምመቐለ