የትግራይ ሴንተራል ኮማንድ አባል አቶ ጌታዉ ረዳ ዲያስፖራ የትግራይ ወጣቶች የትግራይ ህዝብ አሁን ያለበትን ሁኔታ በመገንዘብ ይህን ለመቀየር በትግራይ መንግስትና ህዝብ የቀረበውን ሶስተኛዉ ዙር የመመከት ዘመቻ በድል እንዲጠናቀቅ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ፡፡
አቶ ጌታቸው ረዳ ጥሪውን ያቀረቡት አለም አቀፍ የትግራይ ዲያስፖራ ወጣቶችና በትግራይ መንግስት ዉይይት በዙም ቴክኖሎጂ ትላንት ውይይት መደረጉን ተከትሎ ነው፡፡
በአለም አቀፍ የትግራይ የሃብት መሰባሰብ አዘጋጅነት በትግራይ አሁናዊ ሁኔታና የትግራይ ሶስተኛዉ ዙር የመመከት ዘመቻ በማስመልከት በመላዉ አለም የተዉጣጡ በትግራይ ዲያስፖራ ወጣቶችና በትግራይ መንግስት የተካሄደዉ አለም አቀፍ ዉይይት ደማቅ ተሳትፎ የታየበትና የጋራ መግባባት የተደረሰበት ነበር፡፡
ዉይይቱ የተካሄደዉ እንደ አዉሮፓዉያን አቆጣጠር ጁላይ 23 2022 ሲሆን ከፍተኛ የትግራይ አመራሮችና የትግራይ መንግስ ተወካዮች የተገኙበት እንደነበር ተገልፆል፡፡
በዉይይት መድረኩ የክብር እንግዳ ሁነዉ የተገኙት የትግራይ ሴንተራል ኮማንድ አባል አቶ ጌታዉ ረዳ በውይይቱ የትግራይ ዲያስፖራ ወጣቶች አሁናዊ የትግራይ ሁኔታ በማስመልከት ማብራርያ የሰጡ ሲሆን በተሳታፊዎቹ ለቀረበላቸዉ ጥያቄም መልስ ሰጥተዋል፡፡
የትግራይ ሴንተራል ኮማንድ አባል አቶ ጌታዉ ረዳ ባስተላለፉት መልእክት ዲያስፖራ የትግራይ ወጣቶች አሁናዊ የትግራይ ሁኔታ በመገንዘብ አሁን ላለንበት ሁኔታ ለመቀየር በትግራይ መንግስትና ህዝብ የቀረበላቹሁን የትግራይ ሶስተኛዉ ዙር የመመከት ዘመቻ በድል እንዲጠናቀቅ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በዉይይቱ ላይ የተገኙትፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ ሂወት በበኩላቸዉ እንዳሉት በግራና በቀኝ በርካታ ችግሮች ቢኖሩም በዋና ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርገን በመስራት የማንሻገረዉ ችግር የለም ፡፡ዲፖራ የትግራየ ወጣቶች ይሄን የማድረግ አቅምና ችሎታ አላቹሁ ፡፡በማላት በወጣቶቹ ላይ ያላቸውን እምነት በመግለፅ ቁጭት የተሞላበት መልእክታቸውን አስተላልፏል፡፡
ዓለም አቀፍ የሃብት አሰባሰብ ኮሚቴ አስተባባሪ እና በአውሮፓ የትግራይ መንግስት ተወካይ ዶክተር አክሊሉ ሃይለሚካኤል በበኩላቸው የትግራይ ህዝብ መሪዎቹና አስተዳዳሪዎቹን ሲመርጥ ነባራዊ ሁኔታዎችን በሚገባ የተገነዘበና ሊመጡ የሚችሉ ፈተናዎችም ለመቀልበስ አደራጅቶ ሊያታግለው እንደሚችል አምኖ የገባበት መሆኑን በመገንዘብ አሁንም በትናንሽ አጀንዳዎች ሳንጠመድ ወጣት የትግራይ ዲያስፖራዎች የህዝቡን ድምፅ በመሆን እስካ አሁን ያበረከተው ድርሻ ከፍትኛ መሆኑን በመጥቀስ አሁን ያሉው ሶስትኛ ዙር መመከት የወጣቶቹ ርብርብ እንደሚሻ ተናግሯል፡፡
የውይይይት መድረኩ የተለያዩ ጥያቄዎች ሃሳቦች የቀረበቡበትና አሳታፊ መኖሩን በመጥቀስ ተመሳሳይ የውይይት መድረክ እንዲካሄድ ጥረት እንደሚደረግም በአውሮፓ የትግራይ መንግስት ተወካይ ተጠቅሰዋል፡፡
ፍረ ወይኒ መንገሻ