Home የሀገር ውስጥ ዜና የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በትግራይ አጋጥሞ ያለው ርሃብ ያስከተለው እልቂት ለማስቆም ብሄራዊ አዋጅ...

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በትግራይ አጋጥሞ ያለው ርሃብ ያስከተለው እልቂት ለማስቆም ብሄራዊ አዋጅ ማወጁን አስታወቀ፡፡

152

በትግራይ በ5ት ዞኖች፤ በ32 ወረዳዎችና በ196 ቀበሌዎች ድርቅና የሰብአዊ እርዳታ እጦት የፈጠሩት ከፍተኛ ርሃብ በስፋት እንዳጋጠመ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ገልፀዋል፡፡

በዚህም ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ በትግራይ ኣጋጥሞ ያለው ድርቅና ርሃብ ለመከላከል ክልል ኣቀፍ እንቅስቃሴ ለማወጅ የሚያግዝ ውይይት ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ጋር ውይይት ኣካሄደዋል፡፡

በውይይታቸውም ኣጋጥሞ ያለው ከፍተኛ የርሃብ ኣደጋ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ጌታችው ረዳ በትግራይ የተፈፀመ ጥቃት እያለ ኣሁን ደግሞ ተፈጥራዊ በሆነ መንገድ ሀዝባችን እየጠፋ እና እየተሰቃየ ነው ብለዋል፡፡

ኣሁን ኣጋጥሞ ላለው የርሃብ አደጋ ለመፍታት የሁሉም ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ በጊዜ የለም መንፈስ ሕብረተሰቡን በታማኝነት መንገድ ሊሰራ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ኣያይዘውም ለጋሽ ድርጅቶች 20 በመቶ ብቻ ለሙከራ በሚል ድጋፍ እንደጀመሩ ገልፀው አጋጥሞ ያለው ከፍተኛ የርሃብ አደጋ ለነገ የማይባል ስለሆነ የውስጥ ኣቅማችንን ኣስተባብረን ልንሰራ ይገባል ሲሉ ለታዳሚዎቹ አሳስበዋል ፡፡

በርሃብ ለሚሞተው ህዝባችን የሞት መጠን ለመቀነስ በውስጥም በውጭም የሚገኙ ወገኖች የሚያደርጉት ድጋፍን በማድነቅ በተደራጀ እና በተማከለ መልኩ የሚመራ አሰራርን በመከተል ሁሉን የሚያሳትፍ ትልቅ መድረክ በመፍጠር በአጭር ጊዜ ውስጥ ኮሚቴ እንደሚቋቋም ጠቁመዋል፡፡

ኣስተያየታቸውን የሰጡ የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የትግራይ ጊዜያዊ ኣስተዳደር አሁን ኣጋጥሞ ላለው ርሃብ ህዝብን ከማዳን ስራ ውጭ ሌላ አጀንዳ ሊኖረው አይገባም በማለት ለዚህም በጊዜ የለም መንፈስ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡የውስጥ ኣቅማችንን በማጠናከር የኣለም ኣቀፉ ማህበረሰብ እንዲደርስልን ጎን ለጎን ልንሰራ ይገባል ሲሉም የመድረኩ ተሳታፊዎች ኣስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

#በታደሰ ልጃለም