Home ዜና የአምባገነኑ የኢሳያስ ቡድን  የጀኖሳይድ ዘመቻ በኩናማ ማህበረ-ሰብ እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የአምባገነኑ የኢሳያስ ቡድን  የጀኖሳይድ ዘመቻ በኩናማ ማህበረ-ሰብ እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ፡፡

667

ሆነ ተብሎ በተቀነባበረ ዘመቻ አምባገነኑ የኢሳያስ ቡድን የኩናማ ማህበረ-ሰብን ለማጥፋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የትግራይ መንግስት አስታወቀ።

የትግራይ መንግስት በውጭ ጉዳዮች ፅህፈት ቤቱ በኩል ባወጣው መግለጫ አምባገነኑ ኢሳያስ የትግራይን ህዝብ የማጥፋት ዘመቻውን አካል አድርጐ የኩናማ ማህበረሰብን ከምድር ገፅ ለማጥፋት እየሰራ ነው ብሏል።

አምባገነኑ ኢሳያስ ባለፈው ወር ዳግም በትግራይ ላይ በከፈተው ሁለተኛ ዙር የጀኖሳይድ ጦርነት ዓዲጎሹ በሚባለው ስፍራ በኩናማ ህዝብ ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ አካሄዷል።  

የአምባገነኑ ኢሳያስ ቡድን ከግብረአበሮቹ የፋሽስቱ አብይ ቡድንና የአማራ ሃይሎች ጋር በማበር በትግራይ ህዝብ ላይ ለሁለት ዓመት የዘለቀ ዘግናኝ ግፎች እየፈፀሙ መምጣታቸውን አመልክቷል መግለጫው።

ረሃብን እንደጦር መሳሪያ በመጠቀም፣ በእናቶችና በልጃገረዶች ላይ ወሲባዊና ፆታዊ ጥቃት በመፈፀም እንዲሁም ሰላማዊ ሰዎችን የጅምላ እስር በማካሄድ የሲቪል መሠረተ ልማት አውታሮችን ሆነ ብሎ በማውደም የግልና የመንግስት ንብረቶችን ሃብት በመዝረፍ ግፎች መፈፀማቸውን አስታውቋል የትግራይ ውጭ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

እነዚህ ግፎች ሆነ ብሎ ታስቦባቸው የተፈፀሙና የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ ከተቻለ ዳግም ለማጥፋት ያለሙ እንደሆነም አስታውቋል።

የአምባገነኑ ኢሳያስ ቡድን እንደ አንድ የጀኖሳይድ ዘመቿው አካል በአናሳ ማህበረሰቦች ላይ በተለይ ዳግም ለሁለቱም አገሮች ድንበሮች በሚገኙ የኩናማ ማህበረሰብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመ እንደሆነ አስረድቷል።

ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እንደገና እንዳይደገም የሚለውን ቃል ኪዳን እንዲያከብርና የአምባገነኑን የዘር ማጥፋት ወንጀሉን እንዲያስቆም አሁንም በድጋሚ የትግራይ ህዝብና መንግስት ይማፀናሉ ብሏል። የትግራይ ውጭ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት