Home ዜና የአፍሪካ ህብረት በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም

የአፍሪካ ህብረት በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም

148

ህብረቱ ይፋ እንዳደረገው የፌደራል መንግስት ተወካይ፣ የህወሓት እና በአፍሪካ ህብረት የተሠየሙ አደራዳሪ አካላት እንዲሁም ሌሎች ታዛቢ አካላት በውይይቱ መሳተፋቸውን ገልጿል፡፡

የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አተገባበር ቁጥጥር እና ክትትል ኮሚቴ ባካሄደው ስብሰባ የስምምነቱ አተገባበር ሂደት ያጋጠሙት ፈተናዎችን በማለፍ ለመተግበር የሚያግዙ ዕድሎችን በሚመለከት መወያዩቱን ህብረቱ አመልክቷል፡፡

በስብሰባው ላይ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም አካላት በቆራጥነት እንዲሠሩ፣ ትጥቅ መፍታት እና ሰራዊቱን ወደ ፀጥታ አካላት መቀላቀል ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር፣ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው እንዲመለሱ ማድረግ እና ፖለቲካዊ ውይይት እንዲጀመር ሁሉም አካላት እንዲሰሩ መረዳዳት ላይ መደረሱን ህብረቱ አሳውቋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት በህብረቱ የተሰየመው በኢትዮጵያ የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ክትትል እና ቁጥጥር ኮሚቴ ለሁለት ወራት የስልጣን ግዜው እንዲራዘም ጥያቄ የቀረበ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡ ታጣቂዎች መልሶ ለማቋቋም እና ተዛማጅ ለሆኑ ጉዳዮች የሚውል አድን ሚልዮን ዶላር የአፍሪካ ህብረት መመደቡን ህብረቱ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡

ለተደራዳሪዎች ፣ አደራዳሪዎች አከላትና የፕሪቶርያ ስምምነት ትግበራ ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ሃገራት የአፍሪካ ህብረት ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ስለሺ ሓጎስ