የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ የሆኑት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በቀጠናዊ ጉዳዮች ከትግራይ መንግስት ባለስልጣኖች ለመነጋገር ዛሬ መቐለ ከተማ ገቡ፡፡
የትግራይ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ እንደገለፁት ልዩ መልእክተኛው ከትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል(ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተነጋገረዋል፡፡
ኦባሳንጆ በትግራይ ላይ የተከፈተው የጀኖሳይድ ጦርነት ለማስቆም እና ሰላማዊ መፍትሔ ለማምጣት በተደጋጋሚ ወደ መቐለና አዲስ አበባ እየተመላለሱ የሰላም ጥረት እያደረጉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡