አቶ ጌታቸው ይህን ያሉት የአሜሪካ አምባሳደር በኢትዮጵያ የፖለቲካና ስነቁጠባ ኣማካሪ ጆን ሮቢንሰን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው ።በውይይታቸው ውቅትም በሽግግር ፍትህ ጉዳይና ከመከላከያ ኋይል ውጪ በትግራይ የሚገኙ ወራሪ ሃይሎችን የማስወጣት ጉዳይ አንስተዋል።
በተለይም የወራሪው የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ላይ የፈፀማቸውና እየፈፀማቸው ያሉት ወንጀሎች በኣለም አቀፍ ፍትህ ሊዳኝ እንደሚገባ ፕሬዚዳንተ ጌታቸው ረዳ ለዲፕሎማቱ ገልፀውላቸዋል።በአሁኑ ሰኣት በፌደራል መንግስት ደረጃ ትግራይ ተወካይ እንደሌላትና የህዝቡን ድምፅ ሊያሰማና የህዝቡን ጠቀሜታ መሰረት አድርጎ ሊያወያይ የሚችል ኣካል በሌለበት የሚቋቋመው የሽግግር ፍትህ ትግራይን ያገለለ እንዳይሆን በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ሲሉም ፕሬዚዳንት ጌታቸው አስምረውበታል ።
በተጨማሪ ፕሬዚዳንት ጌታቸው ተፈናቃዮችን በመመለስና የትግራይ ግዛታዊ አንድነት በመጠበቅ ረገድ ማብራርያ የሰጧቸው ሲሆን በፌደራል በኩል የተገለፀው የህዝበ ውሳኔ ጉዳይ ፈፅሞ ሊሆን እንደማይችልም አስረድተዋል።
በምዕራብ ትግራይ፣ በደቡብ ትግራይ፣ ምስራቅና ሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ እንዲሁም በሌሎች የትግራይ አካባቢዎች የሚገኙ ወራሪ ሃይሎች በፌደራል መንግስት እንዲወጡና በአካባዎቹ ያለውን አስተዳደር ፈርሶ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲተካም ፕሬዚዳንቱ አክለው ገልፀውላቸዋል።ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ከዲፕሎማት ጆን ሮቢሰን ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ ክልላዊ፣ ሃገራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች አንስተው የተወያዩ ሲሆን ኣሜሪካ በትግራይም ይሁን በኢትዮጵያ ብሎም በኣፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ አወንታዊ ድርሻ እንደሚኖራት ዲፕሎማቱ መግለጻቸውን ከትግራይ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል ።
#ብርዛፍ ገ/ፃድቃን