በደቡብ ክልል ቡርጂ ወረዳ ሶያማ ከተማ ለግብይት በወጡ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ በተከፈተው የጅምላ ጥቃት 14 ንፁሃን ዜጎች ሲሞቱ ከ30 በላይ ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ጭፍጨፋውን ተከትሎም የቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በመላ ኦሮምያ በንፁሃን ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለው ግድያና መፈናቀል ይቁም በማለት የተቃዉሞ ሰልፍ ኣካሂደዋል ፡፡
ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በኦሮምያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ያሰማራቸው ቅጥረኛ ሰራዊት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ደጋፊ ናችሁ ለሰራዊቱም መሸሸግያ ሆናችሃል በሚል ሰበብ በንፁሃን የኦሮሞ ተወላጆች ላይ እየፈፀመ ያለውን ግድያ እንግልት ቤት ንብረት ማቃጠልና ማውደም ከምንግዜም በላይ ኣጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡
በኦሮምያ የምእራብ #ጉጂ ዞን ስረወ በርጉዳ ወረዳ ነዋሪዎች ለግብይት በወጡበት ወቅት የፋሽስቱ ቡድን ቅጥረኛ ወታደሮች የገበያ ግርግሩን ሽፋን በማድረግ በከፈቱት ድንገኛ ተኩስ 14 ሰላማውያን ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ ወደ 30 የሚጠጉ ንፁሃን ዜጎች ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው OMN ዘግቧል ፡፡
ጉዳዩን ኣስመልክቶ የጉርጂ ወረዳ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ የተፈፀመው ድርጊት ከሰብኣዊነት የወጣ እና በጥብቅ እንደሚያወግዘው በመግለጽ የፋሽሽቱ ቡድን በየቦታው ቅጥረኛ ሰራዊቱን በማሰማራት በንፁሃን ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ ከመፈፀሙ ባሻገር ለዘመናት ተከባብሮና ተዋዶ ይኖር የነበረን ማህበረ-ሰብ በማጋጨት በሃገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት እንዲባባስ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መምጣቱንና በዚህም በርካታ ሰላማውያን ዜጎች በወጡበት እንዲቀሩ ተደርገዋልም ብለዋል፡፡
የፋሽስቱ ቡድን ቅጥረኛ ሰራዊት በገበያ ስፍራ በሰላማውያን ዜጎች ላይ የፈፀሙትን ጭፍጨፋን ተከትሎ የቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በመላ ኦሮምያ በንፁሃን ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለው ግድያና መፈናቀል ይቁም በማለት የተቃዉሞ ሰልፍ ኣካሂደዋል ፡፡
በቡርጂ ልዩ ወረዳ ሶያማ ከተማ ለግብይት በወጡ ንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ጥቃት በመቃወም ሰልፍ የወጡት ተማሪዎቹ የዜጎች በህይወት የመኖር መብት ይከበር በማለት ድምፃቸውን ያሰሙ ሲሆን የፋሽሽቱ ቡድን ቅጥረኛ ሰራዊት በየ ቦታው እየፈፀመው ያለውን ጥቃት ይቁም ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
ፍሬህይወት ተ/መድህን