Home ዜና ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል(ዶክተር) በላኩት ደብዳቤ በትግራይ የሰብአዊ እርዳታ ካለው ችግር አንጻር የሚመጣጠን...

ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል(ዶክተር) በላኩት ደብዳቤ በትግራይ የሰብአዊ እርዳታ ካለው ችግር አንጻር የሚመጣጠን አይደለም ብለዋል፡፡  

984
0

ወደ ትግራይ እየተንጠባጠበ እየገባ ያለው ሰብአዊ እርዳታ መሬት ላይ ካለው ችግር አንጻር የሚመጣጠን አይደለም ሲሉ የትግራይ መንግስት ፕሬዚደንት ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ገለጹ፡፡

የአለም ማህበረ-ሰብ የላከውን ሰብአዊ እርዳታ በተገቢውን መንገድ እንዳይገባ የፋሽስቱ ቡድን ነዳጅ እንዳይገባ በመከልከሉም የገባው ሰብአዊ እርዳታ ወደ ሌሎች የትግራይ አካባቢዎች ማከፋፈል አልተቻለም ብለዋል፡፡

የትግራይ መንግስት ፕሬዚደንት ዶክተር ደብረጽዮን ገብርሚካኤል ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ  ለረዥም ጊዜ ሲስተጓጎል የነበረው የትግራይ ሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየተንጠባጠበም ቢሆን በፈጠርነው ጫና መግባት መጀመሩን ገልፀዋል፡፡

አሁን እየተንጠባጠበ እየገባ ያለው ሰብአዊ እርዳታም መሬት ላይ ካለው ችግር ጋር የማይመጣጠን መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ የሚገኘውን የትግራይ ህዝብ ለመታደግ በተወሰነ መልኩ ወደ ትግራይ የገባው ሰብአዊ እርዳታ ወደ ሌሎች የትግራይ ዞኖችና ወረዳዎች እንዳይከፋፈል የነዳጅ እጦቱ ለስርጭቱ አስቸጋሪ አድርጎታል ያሉት ዶክተር ደብረጽዮን፡፡

ይህም የፋሽስቱ ቡድኑ ሆነ ብሎ የፈጠረው እንቅፋት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የትግራይን ህዝብ እርዳታ እንዲደርሰው ድጋፍ እያደረጉ ላሉት የአለም አቀፍ ማህበረ-ሰብ አባላት ምስጋና ያቀረቡት ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካአል፤ ህዝባችን በከበባና ክልከላ ውስጥ ሆኖ መኖር ስለሌበት አሁን ላይ ቀዳሚው አጀንዳችን የትግራይን ግዛት ነጻ ማውጣት ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም በሰላማዊ መንገድ አልያም በሌላ መልኩ ተግባራዊ እናደርገዋለን ብለዋል፡፡

”  እየተንጠባጠብም ቢሆን ወደ ትግራይ እየገባ ያለው ሰብአዊ እርዳታ በክንዳችን እና በተፈጠረው ጫና ምክንያት ነው እየመጣ ያለው፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን በቂ አይደለም በዓለም አቀፍ የሰብአዊ እርዳታ መመዘኛ እስካሁን ወደ ትግራይ የገባው ሰብአዊ እርዳታ ሶስተኛ ዙር የሚባል ነው ነገር ግን እስከ አለፈው ታህሳስ ወር 2014 ዓም ስድስት ዙር ነበር መግባት የነበረበት፡፡ አሁን ግን  ሶስተኛ ዙር ላይ ነው ያለነው ይህም ባለፈው ጥቅምት ወር ነው የተጀመረው፡፡ አራተኛው፣ አምስተኛውና ስድስትኛው ዙር በስድስት ሳምንታት ውስጥ ይገባል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር ነገር ግን የተገመተው አስፈላጊ የሚባለውን ሰብአዊ እርዳታ እስካሁን ሊመጣ አልቻለም፡፡ 

እስካሁን ወደ ትግራይ የገባው ሰብአዊ እርዳታ ወደ ሌሎች የትግራይ ዞኖችና ወረዳዎች እንዳይከፋፈልም ሆነ ብሎ ነዳጅ እንዳይገባ ከልክለዋል፡፡ ነዳጅ ባለመኖሩ  ምክንያትም እየተንጠባጠበ የገባው የተወሰነ ሰብአዊ እርዳታ በማጋዘን ነው ተከዝኖ ያለው፡፡ መቐለ የገባው ሰብአዊ እርዳታ ወደ ሌሎች ቦታዎች ለማከፋፈል የሚውል ምንም አይነት ነዳጅ የለም፡፡ ይህም ሆነ ተብሎ ነው እየተሰራበት ያለው መጀመሪያ አካባቢ እርዳታ ከልክሎ ነበር አሁን በተወሰነ ደረጃ እርዳታ መግባት ሲጀምር ደግሞ ነዳጅ ከልክለዋል፡፡ ስለዚህ አሁን ትልቁ ችግር ነዳጅ ነው፡፡

ዋና ተልእኮአችን ትግራይን ነፃ ማውጣት ነው አሁን ካለው ክልከላና ከበባ ነጻ እንሁን ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ፣ የትግራይ ሰራዊት፣ የትግራይ ተወላጅ ዲያስፖራዎችና ሌሎች የትግራይ ህዝብ ትግል ደጋፊዎች ፍላጎት እና አላማ ከበባውና ክልከላው በመስበር እያንዳንዱ የትግራይ ግዛት ነጻ መውጣት አለበት የሚል ነው፡፡  ይህንን ለማሳካት ደግሞ በሰላማዊ መንገድ እንዲሆን  አልያም በሌላ መልኩ የምናረጋግጠው ይሆናል  “

በይብራህ እምባየ 

Previous articleየትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ከፋሽስቱ ቡድን ጋር እስካሁን የተካሄደ ድርድር እንደሌለ ተናገሩ፡፡
Next articleየመጀመሪያው የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፊሰር ምትኩ ሃይለን የ2021 የዓለም የእርሻ ሽልማት ሎሬት ብሎ መምረጡን አስታወቀ።