Home Uncategorized ፋሽስት የአብይ ቡድንን ጨምሮ ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ የሚጠቀሙ መንግስታት  ተጠያቂ የሚያደርግ...

ፋሽስት የአብይ ቡድንን ጨምሮ ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ የሚጠቀሙ መንግስታት  ተጠያቂ የሚያደርግ ውሳኔ  ፀደቀ፡፡

1158

የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኝነት ኮሚቴ የሆኑ ሴናተሮች ፋሽስት የአብይ ቡድንን ጨምሮ ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ የሚጠቀሙ አራት መንግስታት  በአሜሪካና አጋሮቿ  ተጠያቂ የሚያደርግ ውሳኔ በአንድ ድምፅ አፀደቀ፡፡

ሴናተሮች በጋራና በአንድ ድምፅ ባስተላለፉት ውሳኔ  የረሃብ ሰቆቋና ቸነፈር እንደጦር መሳሪያ እየተጠቀሙ  የሚገኙ  የፋሽስቱ አብይ ቡድን ጨምሮ የሶሪያ፣ የመንና የደቡብ ሱዳን አገራት መንግስታትን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

Forean Relation የተባለ ድረ ገፅ እንደዘገበው ጦርነት ለምግብ እጥረት ዋነኛው ጠንቅ መሆኑንና በኢትዮጵያ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በየመንና በሶርያ ያሉት መንግስታትበጦርነት ውስጥ አንደሚገኙ በማመልከት የየእርሻ መሳሪያዎችና መሰረተ ልማቶች  በማውደም    የደህንነትና የቢሮክራሲ ማነቆዎችን በመጠቀም በሰብአዊነት ላይ በሚፈፅሙት ግፎች ህዝቦችን ሆን ብለው የማስራብ ፖሊሲ እየተከተሉ ነው፡፡ በዚሁም  ፋሽስቱ የአብይ ቡድንን ጨምሮ አራት መንግስታት ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ  እየተጠቀሙ ነው፡፡ 

ሴናተሮቹ ያስተላለፉት ውሳኔ ረሃብን እንደጦር መሳሪያ የሚጠቀሙ መንግስታትን የሚወግዝና  ተጠያቂ ለማድረግ የአሜሪካ መንግስትና አጋሮቿ እርምጃ  እንዲወስዱ የሚያሳስብ ነው፡፡

ከዩክሬን፣ከሶርያ እስከ ኢትዮጵያ የሚገኙ መሪዎች  የእርሻ መዋቅሮችን በማውደም የሰብአዊ እርዳታን በማስተጓጎል፣ መሰረታዊ ሸቀጣ-ሸቀጦችን  እንዲቋረጡ በማድረግ የጂኦ ፖለቲካ ጥቅሞቻቸውን  ለማስጠበቅ ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ የመጠቀሙ ሁኔታ ተያይዘውታል፤ የሚለው የአሜሪካ ሴኔት ውሳኔ ውሳኔው ግልፅና ሁለቱም ፓርቲዎች የአሜሪካ መንግስት  የአለም-አቀፍ ህግ የመሰረት ድንጋይ የሆነውን  በጦርነት ወቅት ለሰላማዊ ህዝቦች የሚደረግን ጥበቃ እንዲያረጋግጥላቸው  ጥሪ ያስተላለፉበት እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

ሴናተር ጀፍ ማርክለይ በበኩላቸው መንግስታት ጂኦ ፖለቲካል ዓላማቸውን ለማሳካት ሰብአዊ አቅርቦትን መገደብ፤ የእርሻ መሳሪያዎችን ማውደም፤ መሰረታዊ የሆኑ ሸቀጣ ሸቀጦች ገበያ ላይ እጥረት እንዲፈጠር ማድረግ በትግራይ፣ በዩክሬንና፣ ሶሪያ አስከፊ ሁኔታዎች ማያታቸውን  በአብነት አንስተዋል፡፡

የዲሞክራት እና የሪፓበሊክ ፓርቲ አባላት የሆኑት ሴናቶሮች እንዳሉት የአሜሪካ መንግስት ጥሪ የምናቀርብለት ጉዳይ ሰላማዊ ሰዎች በጦርነት ወቅት  ጥቃት እንዳይፈፀምባቸው ዋስትና እንዲኖራቸው ማድረግ  የሚለውን  የመአዝን ድንጋይ  የሆነውን ዓለም አቀፍ ህግ እንዲተገበር  ነው  ሲሉ ያስተላለፉት የውሳኔ ሀሳብ ግልፅ አድርገዋል፡፡

ረሃብን እንደጦር መሳሪያ በመጠቀም በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግፍ እየፈፀሙ የሚገኙ መንግስታት ላይ የአሜሪካ መንግስት እርምጃ የሚወስድበት ጊዜ አሁን ነው ተብሏል፡፡

 በሰላማዊ ሰዎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጥሰት እንዲያበቃ የአሜሪካ መንግስት ስልጣኑንና ሁሉም አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም ግልፅ መልእክት መተላለፉ ይታወቃል ብለዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረትም  በትግራይ የተቋረጡ ስልክ፣ መብራት፣ ባንክ፣ መንገድን ጨምሮ መሰረታዊ አገልግሎቶች መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ከሁለት ቀናት በፊት የጋራ ውሳኔ ላይ መድረሱ ይታወቃል፡፡

መብራህቱ ይባልህ