Home ዜና The economist ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በኢትዮጵያ ለጋዜጣው የሚዘግበውን ጋዜጠኛ ቶም ጋርድነርን በ48...

The economist ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በኢትዮጵያ ለጋዜጣው የሚዘግበውን ጋዜጠኛ ቶም ጋርድነርን በ48 ሰዓታት ውስጥ ከኢትዮጵያ እንዲባረር የወሰደው እርምጃ ተቀባይነት እንደሌለው አስታወቀ፡፡

1439

The economist በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን  በአዲስ አበባ የተቋሙ ወኪል በነበረው ጋዜጠኛ ቶም ጋርድነር ላይ የወሰደው እርምጃ ያልተገባ በማለት አጣጥሎታል፡፡

The economist ባሰራጨው ጋዜጣዊ መግለጫ በፋሽስቱ የአብይ ቡድን የወኪሉ ፕሬስ ፈቃድ መሰረዙን ካሳወቀው በኋላ ቆይቶ በ48 ሰዓታት አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ እንደተነገረው፣ ለዚሁም እንደ ምክንያት የቀረበው የተሳሳተ የዘገባ ስልት መጠቀሙን የአንድን ጋዜጠኛ ከሚጠይቀው ሙያዊ ስነ-ምግባር  በማፈንገጡ  የሚል እንደሆነ አመልክቷል፡፡ ጋዜጠኛ ጋርድነር ጎበዝ ሪፖርተር እና የላቀ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር የተላበሰ  ባለሙያ ነው ሲል ገልጾታል The economist  

እንዲሁም ጋዜጠኛው የፋሽስት የአብይ ቡድንና ግብረ-አበሮቹ  በትግራይ ህዝብ ላይ ያወጁትን ጀኖሳይድ ጦርነትን  ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚዘግባቸው ዘገባዎች ሙያዊ ስነ-ምግባር ጠብቆ፣ በድፍረት እና ከውግንና ነጻ በሆነ መልክ መሆኑንም ነው The economist ያስታወቀው፡፡

የጋዜጠኛ ጋርድነር የተሰረዘው የፕሬስ ፈቃድ እና ይባስ ብሎም፣ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን   የወሰደው የማባረር እርምጃ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያህል የፕሬስ ነጻነት መብት እንደምትጋፋ አማላካች ነው ያለው ዘ ኢኮኖሚስት፣ ባለፈው ዓመት ለኒውዮርክ ታይምስ በሚዘግበው አንድ ጋዜጠኛ ላይተመሳሳይ እርምጃ ወስዶ እንደነበር አስታውሷል፡፡

እንዲሁም ዘጠኝ ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች በፋሽስቱ ቡድን እንደታሰሩና እነዲሰወሩ ተደርገው እንደነበርም ለጋዜጠኘች መብት የሚሟጎተው የሲፒጀን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ ዘ ኢኮኖሚስት በሰጠው መግለጫ አካቷል፡፡

እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2019 የፋሽስቱ የአብይ ቡድን የሰላም ኖቤል ተሸላሚ በነበረበት ወቅት በአገሪቱ ቅድመ ምርመራ (ሰንሰርሺፕን) እንዲያበቃና ኢትዮጵያ ሃሳብን የመግለፅ ነጻነትን በማክበር ረገድ  አቻ አይገኝላትም ሲል ቃል ገብቶ እንደነበር ዘ ኢኮኖሚስት አስታውሷል፡፡ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ሊገዛበት ከቆመው የፕሬስ መርህ ጎን እንዲቆም ዘኢኮኖሚስት አሳስቧል፡፡

በቅርቡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከበረው የፕሬስ ነጻነት ቀን ላይ ከ180 የዓለም አገራት መካከል ኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት መብትን በመጋፋት እና ጋዜጠኞችን በማሰር ቀደም ሲል ከነበረችበት 13ኛ ደረጃ ባንዴ በማሽቆልቆል በ114ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ መገለጹ ይታወሷል፡፡