ወራሪውና ፋሽስቱ የኢሳያስ ሰራዊት ግንቦት 16, 2014 ዓ/ም በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ልዩ ስሙ ገዛ ጊሌ የሚባል ከባቢ አጥቅቶ ለመያዝ ሁለት ብርጌድና አንድ ሻለቃ አሰማርቶ የከፈተው ጥቃት በጀግናው የትግራይ ሰራዊት ከሸፈ።
የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ እንዳስታወቀው ጀግናው የትግራይ ሰራዊት በወሰደው የመከላከልና ፀረ ማጥቃት እርምጃ አንድ የበርጌድ አዛዥ፣ ሶስት የሻለቃ አዛዥ ጨምሮ ከ300 መቶ በላይ የወራሪው ሰራዊት ተደምሰሷል።
ድሽቃ፣ ወታደራዊ የሬድዮ መገናኛ ጨምሮ በርካታ ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያ ተማርኳል።
አረመኔያው የኢሳያስ ሰራዊት የደረሰበትን ምት ተከትሎ ግንቦት 21 እና 22/2014 ዓ.ም የሸራሮ ከተማን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ ሰላማዊ ዜጐች ላይ ጉዳት አድርሷል።