የተባባሩት መንግስታት በጀት ኮሚቴ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የጦር ወንጀል እና ሌሎች ተቀባይነት የለውም ሲል የወቀሰው የተባባሩት መንግስታት አባል ሃገራት የበጀት ኮሚቴ ባካሄደው ጠቅላላ ስብሰባው ላይ እንዳለው፣ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈጸሙ የጦር እና ሌሎች ተያያዥ ወንጀሎችን ለማጣራት ለተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን በጀት የለኝም ማለቱ ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡
የተባባሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ በትግራይ የተፈጸሙትን ወንጀሎች ለማጣራት ለተቋቋመው የባለሙያዎች አጣሪ ቡድን በቅድሚያ በጀትና ቢሮ እንደሚያስፈልገው ገልጾ እንደነበር ያስታወሰው የበጀት ኮሚቴው፣ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ግን ሊደረግ የታሰበው የምርመራ ሂደትና ተፈፀሙ የተባሉትን ወንጀሎች መካዱን ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ከቻይናና ሩሲያ ጀርባ ታዝሎ ገለልተኛ የአጣሪ ቡድንና ሊካሄድ የታቀደውን የማጣራት ስራ ከመጀመሩ በፊት በበጀት እና የተደረገውን ምደባ ባለመቀበል ለማኮላሸት ጥረት እያደረገ መሆኑን አመልክቷል፡፡
የተባባሩት መንግስታት የበጀት ኮሚቴ ግን ኢትዮጵያ በቅርቡ እያቀደው ያለውን ያልተገባ የማስተጓጎል ስራ በመቋወም በቀጣይ ሳምንት በአምስተኛው ስብሰባው ላይ ለአጣሪው ቡድኑ የሚውል በጀት እና አስፈላጊ የቢሮ መዋቅርን የማሟላት ስራ ለማከናወን መወሰኑን አስታውቋል፡፡
በትግራይ በተካሄደው ጦርነት እጅግ ዘግናኝ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ከመፈጸማቸው ባለፈ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ማፈናቀሉን ያስታወሰው መግለጫው፤ የኢትዮጵያ መንግስትና ሸሪኮቹ ግን የተባባሩት መንግስታትን ውሳኔ በበጀትና ሌሎች ምክንያቶችን በመፈጠር እውን እንዳይሆን እየሰሩበት ነው ብሏል፡፡