Home Uncategorized የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የልኡክ ቡድን

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የልኡክ ቡድን

267

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አለም አቀፍ ተራድኦ ድርጀት /ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ/ ዳይሬክተር ስኮት ሆክላንደር የተመራ የልኡክ ቡድን ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ በትግራይ የተቋረጠው የሰብአዊ እርዳታ የሚጀመርበት ሁኔታ እና የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አተገባበር ዙርያ እያጋጠሙ ያሉት ችግሮች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡


በኢትዮጵያ ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ዳይሬክተር ስኮት ሆክላንደር በበኩላቸው የትግራይ ህዝብ ከጦርነቱ በኋላ እያሳለፈው ያለውን የመከራ ህይወት በመገንዘብ እገዛ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አፅንኦት በመስጠት ቀጣይነት ያለውን ግንኙነት በመፍጠር በጤና በእርሻ እና በንፀሁህ የመጠጥ ውሀ አቅርቦት ዘርፎች ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል ፡፡
የአሜሪካ አለም አቀፍ ተራድኦ ድርጀት ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ዳይሬክተሩ ስኮት ሆክላንደር 70 ካሬ መጠልያ ጣብያ እና በሞሞና የጤና ማእከል ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በምግብ እጥረት የተጎዱ ህፃናት ህይወት ለማዳን ድርጅታቸው የተመጣጠነ ምግብ በቀጣይነት እንደሚያቀርብ ተናግረዋል፡፡