Home ዜና የኤስ 3199 ረቂቅ ህግ ፀደቀ

የኤስ 3199 ረቂቅ ህግ ፀደቀ

የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በኢትዮጱያ የዓለም አቀፍ ወንጀል የፈፀሙ ሰዎች ተጠያቂ የሚያደርግ ህጋዊ አሰራር ለማስገባት የኤስ 3199 ረቂቅ ህግ መፅደቁን ተከትሎ የተለያዩ የአሜሪካ ባለስልጣናትና ተፅእኖ ፈጣሪ ሰዎች የተለያዩ አስተያየቶች በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ረቂቅ ህግ ከፀደቀ በትግራይ ህዝብ ላይ የተሳተፉ ወንጀሎኞች ተጠያቂ የሚያደርግ በመሆኑ የሰብአዊ መብት ተማጋቾችና የትግራይ ወዳጆች እና ሌሎች የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች አስተያየታቸው ሲሰጡበት ውለዋል፡፡ የፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ በፈፀመውና እየፈፀመው ባልው የጆኖሳይድ ተግባር ተከትሎ የዓለም ማህበረሰብ በተለይ ደግሞ አሜሪካ የዓለም አቀፍ ወንጀል የፈፀሙ ሰዎች ተጠያቂ የሚያደርግ ህጋዊ አሰራር ለማስገባት ካቀረበቹ ረቂቅ ህጎች ኤስ 3199 እና ኤች አር 6600 እንዲሁም ከአገዋ ተጠቃሚነት መሰረዝ የመሳሰሉት እርምጃዎች ስትወስድ ቆይታለች፡፡ አሁን ደግሞ የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በትግራይ ህዝብ ላይ የሴቶች ፆታዊ ጥቃትና ሰብኣዊ እርዳታ ልክ እንደ ጦር መሳርያ በመጠቀም በፋሽስቱ ቡዱንና ግብረ አበሮቹ እርምጃ ለመውሰድና ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ኤስ 3199 በሰኔት ውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የፀደቀው የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ሲቀባበሉት ውለዋል፡፡ ይህ ተከትሎም የኤሀዋን ግዛት ተወካይ የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባል የሆኑት ሴናተር ጀም ሪሽ የረቂቅ ህግ መሰረታዊ ዓላማ በንፁሃን ዜጎች ላይ ወንጀል የፈፀሙና የሰብኣዊ እርዳታ እንዳይገባ መንገድ የዘጉና በጦርነቱ ላይ እጃቸውን ያስገቡና የተሳተፉ የውጭ ሀይሎች ተጠያቂ የሚያደርግ ህግ ነው፡፡ ስለሆነም ይህ ረቂቅ ህግ መጠየቅ ባለባቸው አካላት በተመለከተ ግጭቱን በመፍታት ረገድ ጠንካራ አቋም እንዳለው መልእክት የሚያስተላልፍ ነው ሲሉ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ሲቀባበሉት ታይተዋል፡፡ በተመሳሳይም ሴናተር ጄፍ ማርክለይ ይህ ረቂቅ ህግ የሰብኣዊ እርዳታ ያለ ምንም መደናቀፍ ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ ሚና ያለው ህግ ነው ሲሉ ያብራሩት ሃሳብ ሲሆን በተለይ ደግሞ በጦርነቱ ላይ ወንጀል የፈፀሙ ሰዎች ተጠያቂ የሚያደርግ በመሆኑ የሰራ ባልደረቦቼ ይህን ረቂቅ ህግ እንዲፀድቅ የበኩላቹ ተራ እንዲወጡ ጥሪ አቀርበዋል፡፡ የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሮቦርት ሜንዴዝ በበኩላቸውም ረቂቅ ህጉ በከፍተኛ ድምፅ ማለፉን ኩራት እንደተሰማቸው ገልፀዋል፡፡ በዛሬው እለት ከፍርድ ውጪ የተደረጉ ግድያዎች፤ የጅምላ ወሲባዊ ጥቃቶች፤ የግዳጅ መፈናቀልና የሰብኣዊ እርዳታ እገዳዎች ልክ እንደጦር መሳርያ ጥቅም ላይ መዋላቸውን በተለመከተ የምንናገርበት ቭቻ ሳይሆን እነዚህ አሰቃቂ ድርጊቶች ለማስቆም እርምጃ የምንወስድበት ነው በማለት በተጨማሪም ድርጊቶቹ የጦር ወንጀሎች በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች የዘር ማጥፋት ሁነው እንዲቆጠሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ውሳኔ እንዲሰጥ የሚጠይቅ የፖሊሲ መዕቀፍ በማዘጋጀት ወንጀለኞቹ ተጠያቂ ለማድረግ ወሳኝ ምእራፍ ነው ያሉቱን የማህበራዊ ሚድያ ዛሌ ሲቀባበሉት ውለዋል፡፡ የፋሽስቱ ቡድን ገና ከጥዋቱም የዓለም ማህበረሰብ ለማደናገር ለድርድር ዝግጁ ነኝ፤ ሰብኣዊ እርዳታ እለቃለው ቢልም መሬት ላይ የሚተያው ሓቅ ግን ለማደናቀፍና ለሌላ ጦርነት ዝግጅት ለማድረግ ነው የሚሉና ሌሎች ስራዎቹ በማህበራዊ ሚድያ እየተጋለጠ ይገኛል፡፡ በሄለን ሃፍቱ

1151