የዛላንበሳ እናቶች ሰቆቃ
በኤርትራ ወታደሮች የጅምላ ፆታዊ ጥቃት ሰለባ ከሆኑት መካከል የ7 ልጆች እናት የሆነችው የትግራይ ዛላንበሳ ከተማ ነዋሪ እናት ዛሬ ላይ ከቀየዋ ተፈናቅላለች:: ሌላኛዋ ወጣት ከወራሪዎቹ ሰይጣናዊ ድርጊት ለመሸሸ የዚህ ሰለባ ናት:: የአምበገነኖች ቁንጮ የሆነው በኤርትራው ኢሳያሰ አፈወርቂ በትግራይ ጠል ተረት ተረት ያደገውና ኑሮውን ከቀበሮ ጉድጓድ ሳይላቀቅ ያደገው ሰራዊት፣ በትግራይ ምድር ለዓለማችን እንግዳ የሆኑ አሰቃቂ ግፎችን ፈፅመዋል:: ዛሬ ላይ ቀየዋን ጥላ ከመሰደዷ በፊት በተደጋጋሚ ወረራ የደቀቀችው ዛላምበሳ ከተማ ነዋሪ የነበረችው የ7 ልጆች እናት ሕዳር 3/2013 ዓ/ም ሰለገጠማት ዱቡዳ ለትግራይ ቴሌቪዥን እንዲህ ስትል ገልፃልች:: ያኔ ሳምንት ያስቆጠረውን ጦርነት እንዳመጣህ መልስልን ስትል ፈጣሪዋን ተማፅና ወደ ቤቷ ትመለሳለች:: እንደወትሮው የቤትዋን በር ከፍታ ወደ ውስጥ ስትገባ የገጠማት ነገር ግን በህይወቷ ኣይታው የማታውቀው እጅግ አስድንጋጭ እና አሳዛኝ ክስተት ትላንት የተፈጠረ ያህል ታሰታውሰዋለች:: በሰማችው አስድንጋጭ አረመኔያዊ ተግባር ከዛላምበሳ ወደ አዲግራት የሸሸችው ሌላኛዋ ወጣትም ከእነ ሰይጣናዊ ተግባራቸው ተከትለዋት ወደ አዲግራት ከተማ በገቡት የኤርትራ ወታደሮች በሌሎች ላይ ሲፈፅሙት የተመለከተችውና የፈራችው ነውረኛ ተግባራቸው አልቀረላትም:: እነኚህን እንደ ምሳሌ አነሳን እንጂ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ሀይሎች በትግራይ ምድር ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ፃታዊ ጥቃት ፈጣሪ ይቁጠረው:: በዘንድሮው #ዓለም አቀፍ የማርች 8 የሴቶች ቀን የትግራይ ሴቶች ሰቆቃ የአለም አጀንዳ ሆኖ መከበሩ መልካም ቢሆንም የትግራይ እንስቶች እምባ ለማበስ ወንጅለኞቹ ወደ ሕግ ማቅረብ ይገባል ብለዋል የጥቃቱ ሰለባዎች። በሄለን ወ/ ዮሃንስ